የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አብዲ መሀሙድ ኡመር ወደ ሀገሪቷ ርዕሰ መዲና አቀኑ

አዲስ አበባ(Cakaaranews)ማክሰኞ፤ሚያዚያ 16/2010ዓም.የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አብዲ መሀሙድ ኡመር በዛሬው እለት ለቀድሞ  ጠቅላይ ሚንስትር ክቡር አቶ ሀይለማርያም ደሳልኝ የሚደረግላቸዉን ደማቅ የሽኝት ፕሮግራም ስነ-ስርዓት ለይ ለመካፈል ወደ ሀገሪቷ ርዕሰ መዲና አዲስ አበባ አቀኑ፡፡ በሽኝት ሥነ-ስርዓቱ ላይ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ፣ የክልል ፕሬዝዳንቶች፣ ከፍተኛ የፌዴራል መንግስት ሀላፊዎች፣ አምባሰደሮች፤ ዲፕሎማቶችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የሚካፈሉ ሲሆን የሽኝት ስነ ስርዓቱም  በብሄራዊ ቤተመንግስት የሚደረግ ይሆናል፡፡

   

 

 

የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ምክርቤት መደበኛ ያልሆነ ስብሰባ እንደሚያካሄዱ ተገለጸ (2)

ጅግጅጋ(Cakaaranews) ቅዳሜ፤ሚያዝያ 13/2010ዓም.የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት ምክርቤት አላት  በ2010ዓም በክልሉ ይካሄድ የነበረው የአከባቢው ምርጫ አስመልኪቶ በቀጣይ ቀናት መደበኛ ባልሆነ  መልኩ አስቹኳይ ስብሰባ አካሄዶ የምርጫው ወቅት እንደሚያዘዋወሩ የም/ቤቱ ጽ/ቤት አስታውቋል።

በተጨማሪም የ 9ኙ ክልል መንግስታትና የሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ም/ቤቶች በ2010ዓም በየክልሉ ይካሄድ የነበረውን የአከባቢው ምርጫ ወቅት የሚያራዘሙበት መደበኛ ያልሆነ ስብሰባዎች እንደሚያሄዱም የጽ/ቤቱ አስረድቷል።የወረዳና የቀበሌ ምርጫ ወይም የአከባቢ ምርጫ የማካሄድ ውሳኔ በክልሉ ም/ቤት የሚመለከት ጉዳይ እንደሆነና የምርጫው ወቅት ስለደረሰ፤ ምርጫው በአጠቃላይ ሀገሪቱ  በአንድ ወቅት ለማካሄድ እንደተወሰኔም የኢ.ሶ.ክ.መ. ም/ቤት ጽ/ቤቱ አስታውቋል።

የኦሮሚያ ክልል መንግስት ፕሬዝዳንት የመልሶ ማቋቋም ኮሚቴ አቋቋማል

አዲስአበባ(Cakaaranews)እሮብ፤ሚያዝያ 10/2010ዓም. የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ም/ቤት(ጨፌ)ከቀናት በፊት ያባካ መደበኛ ገባኤ የክልሉ ርዕሰመስተዳደር ክቡር አቶ ለማ መገርሳ ለም/ቤቱ ያቀረቡት ሪፖርት ከኦሮሚያ ክልል የተፈናቀሉ የኢትዮጵያ ሶማሌ ወገኖች መልሶ የሚያቋቋሙ ኮሚቴ ማቋቋሙን ገልጿል። የመልሶ ማቋቋም ኮሚቴ አባላቱ ከክልሉ ከፍተኛ አመራር አካላትና ከልሉ ም/ቤት አባላት የተወጣጡ ሲሆን በቅርቡ  በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የሚገኙና በግጭቱ ሳቢያ ከኦሮሚያ ክልል የተፈናቀሉ የኢትዮጵያ ሶማሌ ተፈናቃዮችን ወደ ኦሮሚያ እንደሚወስዱም ይጠበቃል።

 ይህ ሰናይ እርምጃ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰመስተዳደር አቶ ለማ መገርሳ ስልጣና ጀግንነት በተሞላ በወወሰኑት ውሳኔ ተከትሎ የክልሉ መሪ ጅርጅትና መንግስት ተግባራዊ እያደረጉ መሆኑን ያሳያል።

በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት ከአሁን በፊት እንዲህ ውሳኔዎች በማሳለፍና ተግባራዊ በማድረጉ ከኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የተፈናቀሉ በርካታ የኦሮሚያ ክልል ተወላጆች ወደ ቀድሞ ቄያቸው ተመልሶ በአሁኑ ወቅት በአከባቢያቸው በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መደበኛ ስራቸው ተሰማርቶ በሰላም እየሰሩ ይገኛሉ።የኢትዮጵያ ክልል ሶማሌ መንግስት የክልሉ ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አብዲ መሀሙድን ጨምሮ የኦሮሚያ ክልል መንግስት ብሎም የክልሉ ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ለማ መገርሳ መልካም ውሳኔን ደስተኛ መሆናቸው አስታውቀዋል።

 በመሆኑም በሞያሌ የተከሰተው ችግር የሁለቱም ብሔሮችና የሁለቱ ክልሎች የማይወከል አጸያፍ ድርግት መሆኑንና ከጥንት ጀምሮ ለዘመናት በሰላም አብሮ የኖሩ የኦሮሞና ሶማሌ ህዝቦች የቆየውን ባህልና እሴት ለማፍረፍ እንዲሁም በቅርቡ ከሁለቱ ክልል መሪዎች የተደረሰው የዘላቂ መፍትሄ ስምምነት እንዳይሳካ የፈለጉት ፅንፈኛና ጥቅመኛ ግለሰቦች ሴራ የተፈጸመ አስነዋሪ ተግባር መሆኑንም የኢትዮጵያ  ሶማሌ ክልል መንግስት አስታውቋል።

 

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የቀረቡትን የካቢኔ አባላት ሽግሽግና ሹመትን አጸደቀ

አዲስአበባ( cakaaranews)ሀሙስ፤ሚያዚያ 11/2010 ዓ.ም. የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት  የ10 አዳዲስ ሚኒስትር ሹመት ፀደቀ፡፡የኢፌዴሪ መንግሥት በአሁኑ ወቅት ከህዝቡ የቀረበበትን ጥያቄ ተገቢ ምላሽ ለመስጠት በተደረገው ግምገማ መሠረት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የ10አዳዲስ ሚኒስትርችና የ6 ሽግሽግ ያደረጉ ሚኒስትሮችን ለተከበረው ምክር ቤት አቅርበዋል፡፡ የሴቶችን ተሳትፎ ለማረጋገጥ፣ መልካም አስተዳደርና የሙስና ችግር ለመፍታት መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በዚህም መሰረት ከተሾሙ ሚኒስትሮች መካከል ሁለቱ ከኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል/ከኢሶህደዴፓ ሲሆኑ እነሱም፡-

1. /ኡባመሀመድ ………የመገናኛናኢንፎርሜሽንሚንስትር

2. አቶአህመድሺዴየመንግስትኮሙዪኒኬሽንጉዳዮችፅህፈትቤት ኃላፊሚኒስትር 

3. አቶሽፈራውሽጉጤ …….የግብርናእናየእንስሳትሃብትሚንስትር
4.
አቶሲራጅፈጌሳ……….የትራንስፖርትሚንስትር
5.
/ሂሩት/ማርያም…….የሰረተኛናማህበራዊጉዳዮችሚንስትር
6.
አምባሳደርተሾመቶጋ………………የመንግስትየልማትድርጅቶችሚንስትር 
7.
አቶኡመርሁሴን………….በሚኒስትርማእረግየኢትዮጵያገቢዎችእናጉምሩክ 
ባለስልጣንዋናዳይሬክተር
8.
/አምባቸውመኮንን……የኢንዱስትሪሚንስትር
9.
አቶሞቱማመቃሳ…………….የሀገርመከላከያሚንስትር
10.
/ፎዚያአሚን…………….የባህልናቱሪዝምሚንስትር
11.
አቶጃንጥራርአባይ…………. የከተማልማትናቤቶችሚንስትር
12.
አቶመለሰአለሙ……………..የማዕድናኢነርጂሚንስትር
13.
አቶብርሃኑጸጋዬ…………….. /አቃቤህግ
14.
/ያለምጸጋዬ……………..የሴቶችናህጻናትሚንስትር
15.
አቶመላኩአለበል…………….የንግድሚንስትር
16.
/አሚርአማን…………......የጤናጥበቃሚንስትር

 

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የቀረቡትን የካቢኔ አባላት ሽግሽግና ሹመትን አጸደቀ፡፡ጠቅላይ ሚንስትሩ የ6 ሚንስትሮችን የስልጣን ሽግሽግ፤ የ10 ሚንስትሮች አዲስ ሹመት ዛሬ በህዝብ ተወካዮች ምክር አቅርበው ጸድቆላቸዋል፡፡የሚንስትሮቹ የስልጣን ሽግሽግና ሹሙት የተካሄደው በዋናነት የህዝብን ጥያቄና ቅሬታ እንዲሁም ሙስናና ኪራይ ሰብሳቢነትን ችግር ከመፍታት አንፃር ካላቸው አቅም አኳያ መሆኑን ጠቅላይ ሚንስትሩ አብራርተዋል፡፡እንዲሁም የአቅም ክፍተት ኖሯቸው እራሳቸውን ለመለወጥና ለመማር ዝግጁ የሆኑ ሚንስትሮች በካቢኔ ዝርዝር ውስጥ ተካተዋል ብለዋል፡፡የህዝብን አገልግሎት ፍላጎት ለሟሟላት ዋንኛ ትኩረታቸው በመሆኑ ይህ ሊታለፍ የማይቻል መሆኑን ማወቅ እንዳለባቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ አሳስበዋል፡፡

 

የመንግስትን ሀብትና ጊዜን የማባከን ሂደትን በመቅረፍ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት ሊወጡ ይገባል ነው ያሉት፡፡ከሁሉም በላይ ግን ህዝቡን በማማረር በመንግስት ላይ የከረረ ተቃውሞዋቸውን እንዲያነሱ የሚያደርጉትን የሙስናና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ የመጀመሪያ ስራቸው ማድረግ እንዳለባቸውም አሳስበዋል፡፡የተሾሙት ሚኒስትሮች ቃለ መሀላ ፈጽመዋል፡፡ከዚህ በተጨማሪም የህዝብ ተወካዮች ም/ቤቱ ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈጉባኤ አደርጎ መርጠዋል።

ከረመዳን ወር በፊት የሚካሄደው የመንግስትና ህዝብ የጋራ መድረክ በዘንድሮ በአውበሬ ወረዳ እንደሚዘጋጅ ተገለጸ (2)

ጅግጅጋ(Cakaaranews)ማክሰኞ፤ሚያዝያ 9/2010..እንደምታወቀው በየአመት ረመዳን ወር ሳይገባ ከቀናት በፊት የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ህዝብና መንግስት ለቀናት የሚዘልቅ የጋራ ምክክር መድረክ ይካሄዳል።በመሆኑም ከረመዳን ወር በፊት የሚካሄደው የክልሉ መንግስትና ህዝብ የጋራ መድረክ በዘንድሮ በፋፈን ዞን በአውበሬ ወረዳ እንደሚዘጋጅ መንግስት አስታውቀዋል።

በተጠማሪም ጉባኤው በአውበሬ ከተማ 3ቀናት የሚካሄድ ሲሆን ከግንቦት አንድ እስከ ግንቦት 3/2010ዓም የሚዘልቅ ከመሆኑ ባሻገር ከረመዳን ወር 3ቀናት ያህል እንደምቀድምም ታውቀዋል። የጉባኤው አዘጋጅ ኮሚቴ በዚህ ሳምንት ውስጥ ወደ አስተናጋጁ ከተማ አውበሬን ያመራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

Amharic News 08_09_10


Amharic News 07_09_10


Amharic News 05_09_10Amharic News 04_09_10Amharic News 26_08_10


Amharic News 25_08_10


Amharic News 24_08_10Amharic News 23_08_10Amharic News 22_08_10


Amharic News 21_08_10Amharic News 20_08_10


Amharic News 19_08_10Amharic News 18_08_10


Amharic News 17_08_10