የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የቀረቡትን የካቢኔ አባላት ሽግሽግና ሹመትን አጸደቀ

አዲስአበባ( cakaaranews)ሀሙስ፤ሚያዚያ 11/2010 ዓ.ም. የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት  የ10 አዳዲስ ሚኒስትር ሹመት ፀደቀ፡፡የኢፌዴሪ መንግሥት በአሁኑ ወቅት ከህዝቡ የቀረበበትን ጥያቄ ተገቢ ምላሽ ለመስጠት በተደረገው ግምገማ መሠረት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የ10አዳዲስ ሚኒስትርችና የ6 ሽግሽግ ያደረጉ ሚኒስትሮችን ለተከበረው ምክር ቤት አቅርበዋል፡፡ የሴቶችን ተሳትፎ ለማረጋገጥ፣ መልካም አስተዳደርና የሙስና ችግር ለመፍታት መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በዚህም መሰረት ከተሾሙ ሚኒስትሮች መካከል ሁለቱ ከኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል/ከኢሶህደዴፓ ሲሆኑ እነሱም፡-

1. /ኡባመሀመድ ………የመገናኛናኢንፎርሜሽንሚንስትር

2. አቶአህመድሺዴየመንግስትኮሙዪኒኬሽንጉዳዮችፅህፈትቤት ኃላፊሚኒስትር 

3. አቶሽፈራውሽጉጤ …….የግብርናእናየእንስሳትሃብትሚንስትር
4.
አቶሲራጅፈጌሳ……….የትራንስፖርትሚንስትር
5.
/ሂሩት/ማርያም…….የሰረተኛናማህበራዊጉዳዮችሚንስትር
6.
አምባሳደርተሾመቶጋ………………የመንግስትየልማትድርጅቶችሚንስትር 
7.
አቶኡመርሁሴን………….በሚኒስትርማእረግየኢትዮጵያገቢዎችእናጉምሩክ 
ባለስልጣንዋናዳይሬክተር
8.
/አምባቸውመኮንን……የኢንዱስትሪሚንስትር
9.
አቶሞቱማመቃሳ…………….የሀገርመከላከያሚንስትር
10.
/ፎዚያአሚን…………….የባህልናቱሪዝምሚንስትር
11.
አቶጃንጥራርአባይ…………. የከተማልማትናቤቶችሚንስትር
12.
አቶመለሰአለሙ……………..የማዕድናኢነርጂሚንስትር
13.
አቶብርሃኑጸጋዬ…………….. /አቃቤህግ
14.
/ያለምጸጋዬ……………..የሴቶችናህጻናትሚንስትር
15.
አቶመላኩአለበል…………….የንግድሚንስትር
16.
/አሚርአማን…………......የጤናጥበቃሚንስትር

 

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የቀረቡትን የካቢኔ አባላት ሽግሽግና ሹመትን አጸደቀ፡፡ጠቅላይ ሚንስትሩ የ6 ሚንስትሮችን የስልጣን ሽግሽግ፤ የ10 ሚንስትሮች አዲስ ሹመት ዛሬ በህዝብ ተወካዮች ምክር አቅርበው ጸድቆላቸዋል፡፡የሚንስትሮቹ የስልጣን ሽግሽግና ሹሙት የተካሄደው በዋናነት የህዝብን ጥያቄና ቅሬታ እንዲሁም ሙስናና ኪራይ ሰብሳቢነትን ችግር ከመፍታት አንፃር ካላቸው አቅም አኳያ መሆኑን ጠቅላይ ሚንስትሩ አብራርተዋል፡፡እንዲሁም የአቅም ክፍተት ኖሯቸው እራሳቸውን ለመለወጥና ለመማር ዝግጁ የሆኑ ሚንስትሮች በካቢኔ ዝርዝር ውስጥ ተካተዋል ብለዋል፡፡የህዝብን አገልግሎት ፍላጎት ለሟሟላት ዋንኛ ትኩረታቸው በመሆኑ ይህ ሊታለፍ የማይቻል መሆኑን ማወቅ እንዳለባቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ አሳስበዋል፡፡

 

የመንግስትን ሀብትና ጊዜን የማባከን ሂደትን በመቅረፍ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት ሊወጡ ይገባል ነው ያሉት፡፡ከሁሉም በላይ ግን ህዝቡን በማማረር በመንግስት ላይ የከረረ ተቃውሞዋቸውን እንዲያነሱ የሚያደርጉትን የሙስናና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ የመጀመሪያ ስራቸው ማድረግ እንዳለባቸውም አሳስበዋል፡፡የተሾሙት ሚኒስትሮች ቃለ መሀላ ፈጽመዋል፡፡ከዚህ በተጨማሪም የህዝብ ተወካዮች ም/ቤቱ ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈጉባኤ አደርጎ መርጠዋል።

Amharic News 21_11_10


Amharic News 20_11_10Amharic News 19_11_10


Amharic News 18_11_10


Amharic News 17_10_10Amharic News 16_10_10Amharic News 15_10_10


Amharic News 14_10_10


Amharic News 13_10_10Amharic News 12_10_10Amharic News 11_10_10