ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ በጅግጅጋ ከተማ ሲያካሄድ የነበረው የተማሪዎች ዉድድርና ስምፖዝየም አጠናቀቀ

ጅግጅጋ (Cakaaranews) ሀሙስ፤ ሚያዚያ 25/2010ዓ.ም. የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ማህበር ከዩኒቨርሲቲው አስተዳደር እና ከክልል ትምህርት ቢሮ ጋር በመተባበር  ለጅግጅጋ ከተማ ተማሪዎች የፓናል ዉይይት እና ቃለ መጠይቅ መድረክ አዘጋጅተዋል።

በክልሉ ትምህርት ቢሮ መሰብሰቢያ አዳራሽ በተካታታይ ቀናት ሲካሄድ የነበረው የተማሪዎች ዉድድር እና ፓናል ዉይይት በዛሬው ዕለት በዉድድሩ ፍፃሜ የተገናኙት የጅግጅጋ ሞዴል ስኩል ት/ቤት እና ጂግጂጋ መሰናዶ ት/ቤት  ተገኝተዋል። በዉድድሩ ማጠናቂያ መድረክ ላይም የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክና ምርምር ም/ፕረዜዳንት ፤የክልሉ ትምህርት ቢሮ ም/ቢሮ ሃላፊ᎓ የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ማህበር ተወካዮችና የተወዳዳሪ ት/ቤቶች ርዕሰ መምህራን ተገኝተዋል፡፡

በመድረኩ ላይ መዝጊያ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ትምህርት ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ አቶ መሀሙድ አህመድ ኑር “የዚህ ዓይነት መድረኮች ለታማሪዎች ያላቸው ሃገራዊ ፋይዳዎች የላቀ እንደሆነና ለወደፊትም  የተማሪዎች ዉድድር እና ስምፖዝየም ዉይይቶች በሌሎች ት/ቤቶች ላይ እንዲዳረሱ እንዲሁም የሀገራችን የትኩረት አቅጣጫ የሆነውን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ትምህርትን ትኩረት እንደሚሰጠ ገልጿል፡፡ በሌላ በኩል የጂግጂጋ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክና ምርምር ም/ፕረዜዳንት አቶ ኢልያስ ኡመር  ዉድድር መድረኩ ለታዳጊ ተማሪዎቻችንን ከፍተኛ ፋይዳ መኖሩንና ተማሪዎችን የሚያነቃቃና የእርስ በእርስ ፉክክርን የሚፈጥር ነው ብሏል፡፡ ይህ ደግሞ በጂግጂጋ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ማህበር ተነሳሽነት የተዘጋጀ እንደሆነና መመስገን እንደሚገባቸውም ም/ፕረዜዳንቱተናግረዋል፡፡  ለወደፊትም ዩኒቨርሲቱ ለክልሉ ማህበረሰብ እንዲህ አይነት ፕሮግራሞችን በፍላጎታቸው በዩኒቨርሲቲው ተነሳሽነት እንደሚያመቻቹ  የጂግጂጋ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክና ምርምር ም/ፕረዜዳንት አቶ ኢልያስ ኡመር  ገልጿል፡፡

በመጨረሻም የዉድድሩ አሸናፊ የሆኑት በአንደኛነት የጂግጂጋ ሞዴል ስኩል ት/ቤት እና በሁለተኝነት  የጅግጅጋ መሰናዶ ት/ቤት ሲሆኑ በጂግጂጋ ዩኒቨርሲቲና በክልሉ ትምህርት ቢሮ የተዘጋጀላቸው ሽልማቶች ከዕለቱ ዕንግዳ ተበርክቶላቸዋል፡፡

 

 

Amharic News 08_09_10


Amharic News 07_09_10


Amharic News 05_09_10Amharic News 04_09_10Amharic News 26_08_10


Amharic News 25_08_10


Amharic News 24_08_10Amharic News 23_08_10Amharic News 22_08_10


Amharic News 21_08_10Amharic News 20_08_10


Amharic News 19_08_10Amharic News 18_08_10


Amharic News 17_08_10