የኢትዮጵያ ሶማሊ ህዝብ የተገኘውን ሰላም እና ልማት ውጤቶች አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ቀረበ

አውበሬ(cakaaranews)ማክሰኞ፤ግንቦት 7 ቀን፤2010ዓ.ም.በአውበሬ ወረዳ በተዘጋጀው 12ኛው የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የሠላም ፣ የልማት እና የመልካም አስተዳደር  የህዝብ እና የመንግሥት የጋራ ምክክር መድረክ ላይ የተገኙ ተሳታፊዎች የተገኘውን ሠላም እና ልማት ውጤቶች አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ቀርቧል። በዚህ የህዝብ እና የመንግሥት የጋራ ምክክር መድረክ ከክልሉ 11 ዞኖች፤ከ93ቱ ወረዳዎችና ከ6 የከተማ አስተዳደሮች የተገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች የሃገር ሽማግሌዎች ፣ የጎሳ መሪዎች፤ የእምነት አባቶች፤ሴቶች ወጣቶች፤የዲያስፖራ አባላት፤ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ሃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው የክልሉ ተወላጆች የተገኙ ሲሆን ባለፉት 8 ዓመታት የተገኙት የልማት ድሎችን ለማስቀጠል ከመንግሥት ጋር አብረው እንደሚሠሩም ቃል የገቡበት ታላቅ ጉባኤ ነበር።

በተለይም ከክልሉ ሚዲያ  ጋር ቆይታ ያደረጉት የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አብዲ መሀሙድ ኡመር በዚህ የጋራ መድረክ መንግሥት የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በወሰዳቸው ቁርጠኛ ተግባራት ባለፉት 8 ዓመታት የተገኙ ለውጦችና ዕድገቶች አበረታች መሆናቸው የገለፁ ሲሆን ይሄን የተገኘውን ሁለንተናዊ እድገት አጠናክሮ ለማስቀጠል እንደዚህ ዓይነት ታላቅ የመንግሥት እና ህዝብ የጋራ መድረክ አስፈላጊነቱን  አብራርቷ።

በተጠማሪም የክልሉን ሠላም እና ልማት የማይወዱ አካላት ባለፈው ሳምንት ፀብ ለማጫር እና ለማደፍረስ በማሰብ የተቃጣውን አፍራሽ ተልዕኮ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ህዝብ በተለያዩ ዞኖች፤ ከተማ አስተዳደሮች እና ወረዳዎች በነቂስ በመውጣት  ከመንግሥት ጋር መቆሙን ያሳየበት ታላቅ የድጋፍ ሠልፍ ህዝቡ ከመንግሥት ጋር መቆሙን የሚያሳይ መሆኑንም ክቡር ፕረዝዳንቱ አስገንዝቧል።

በ12ኛው ታላቅ የህዝብ እና መንግሥት ጉባኤ ላይ በክልሉ መንግስት በ2010ዓ.ም ባጄት አመት የ9 ወራት የሥራ እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት የቀረበ ከመሆኑ በዘለለ ክልሉ በሠላም ፣ በልማት እና በመልካም አስተዳደር እንዲሁም በዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታና በህዳሴ ትራንስፎርሜሽን  የታዩ ከፍተኛ ለውጦችን አጠናክሮ እንዲቀጥሉ ክቡር ፕሬዝዳንቱ ጥሪ አቅርበዋል።

Amharic News 21_11_10


Amharic News 20_11_10Amharic News 19_11_10


Amharic News 18_11_10


Amharic News 17_10_10Amharic News 16_10_10Amharic News 15_10_10


Amharic News 14_10_10


Amharic News 13_10_10Amharic News 12_10_10Amharic News 11_10_10