ማሳሰቢያ!!

ጅግጅጋ(Cakaaranews) መክሰኞመስከረም 30,2010.ም ማሳሰቢያ!! የፌስቡክ ተጠቃሚዎች በሙሉ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ አብዲ መሀሙድ ኡመር በሚል ስም የተከፈተው የፌስቡ ፡ክፔጅ፣ ትክክለኛ የፕሬዚዳንቱ የፌስቡክ ፔጅ አለመሆኑን እየሳወቅን፤ ይህን የተሳሰተ መረጃ በማሰራጨት፣ ህብረተሰቡን ለማሳሳት በፕሬዝዳንቱ ስምየፌስቡክ ፔጅ የከፈተው ግለሰብ አሁን በሀገራችን ያለውን ልማትና እድገት ቀጣይነት የማይፈልግ የብሄር ብሄረሰቦችንና ህዝቦችን አብሮ የመኖር የማይቀበል አጭበርባሪ ግለሰብነው፡፡ ይህን ፔጅ የከፈተው ግለሰብ ወቅታዊ ሁኔታን በመጠበቅ በፕሬዚዳንቱ ስም ህዝቡን የተሳሳተ መረጃ በማስጠት ላልተፈለገ ድምዳሜ እንዲደርስ ስራዬ ብሎ የሚሰራ ግለሰብነው፡፡

ስለሆነም የተከበራቹ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች በክቡር ፕሬዚዳንቱ ስም ትክክለኛው የፕሬዚዳንቱ አካውንት አለመሆኑን እየገለፅን፤ በዚህ ፌስቡክ የሚሰጡ መረጃዎች ትክክለኛነት እንዲታረጋግጡ እንጠይቃልን፡፡