10ኛው የኢ.ፈ.ደ.ሪ. ሰንደቅ አለማ በዓል ቀን በጅግጅጋ ከተማ በድምቀት ተከብሯል!!

ጅግጅጋ (Cakaara News) ሰኞ, ጥቅምት, 06  2010ዓም  “ራዓይ ሰንቀናል ለላቀ ድል ተነስተናል’’ በሚል መሪ ቃል በዛሬው ዕለት10ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን ክብረ በዓል  በደማቅ ስነሥርዓት ክልል ደረጃ በጅግጅጋ ስታድዮም ተከበሯል፡፡

በዚህ ክብረ በዓል ለይ የተደሙት የክልሉ ከፍተኛ አመራር አካላት የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ መሀሙድ ኡመር፣ የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንቶች፣ የክልሉ ቢኔ አባለት፣ የመንግስት ሰራተኞች፣ የሀገር መከላክያ ሰራዊት፣ የክልሉ ፀጥታ አካላት፣ ሀገር ሽማግሌዎች፣ የጅግጅጋ ከተማ ነዋሪዎች፣ የኃይማኖት አባቶች ተሳትፏል፡፡

በበዓሉ ላይ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አብዲ መሀሙደ ኡመር  ለመላው የኢትዮጵያ ህዝቦችና የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ህዝብን ለ10ኛው የሰንደቅ ዓለማ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸዉን አስተላልፏል፡፡ የኢትዮጲያ ቤሔራዊ ሰብደቅ አላማችን ስናከብር ለሀገራችን በሔሮች ቤሔሮችብሔረሰቦችና ህዝቦች ማንነት  ውድ ህይወታቸው ለፀዉት ሰማዕታት ክብር መስጠት እንደሚገባም ርዕሰመስተዳደሩ አሳስቧል::

ከዚህ በተያያዜም ርእሰ መስተዳድሩ ባስተላለፉት መልዕክት እንዳሉት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ዕውን ለማደረግ ውድ የህዝብ ልጆች ባካሄዱት እልህ አስጨራሽና መራራ ትግል መተኪያ የሌለውን ህይወታቸውን ማሳለፋቸውን መገንዘብ ይገበናል ብለዋል።

የሰንደቅ ዓላማ ቀን ስናከብር ከሰንደቅ ዓላማው ላይ የሚቀመጠው ብሔራዊ ዓርማ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች፣ ህዝቦች እኩልነትናሃይማኖቶች ነፃነትአብሮ ለመኖር ያላቸው ብሩህ ተስፋ የሚያንፀባረቅ መሆኑን ማስተዋል ይጠብቅብናል፡፡

የአዲሲቷ ኢትዮጵያ ትውልድ መሆናችን  በልባችን ሰንደቅ ዓላማችን መቅረጽ ይኖርብናል ነው ያሉት በሌላ በኩል አቶ አብዲ መሀሙድ ሰንደቅ አላማችን ከፍ አደርገን በማውለብለብ ደህንነትን ለማሸነፍ የጀመር ነው ትግል ለማሳካት ሁላችንም በሰንደቅአላማችን ፊት ቃል የሚንገባበት መሆኑን ተናግሯል:: ላለፉት አመታት በሰንደቅ አላማችን ሥር ሆንን ዘርፈብዙ  እድገት ማስመዝገብ ችለናል ነው ያሉት በቀጣይም የሀገራችን ህዳሴ እውን ለማድረግና የነጌ ተስፋችን መሰነቅ የሚንችለው በሰንደቃችን ሥር መሆኑንና ሰንደቅ አላማችን ማክበርና ማስከበርም የሁላችንም ኃላፊነት መሆኑን አስገንዝቧል::

በተጨማሪም ርዕስመስተዳደሩ በኢትዮጲያ ሶማሌና በኦሮሚያ ክልሎች አዋሰኝ አከባቢዎች በተፈጠረው ግጭት በሰላምና በውይይት ለመፍታት ዝግጁ መሆናቸውና ሁለቱ ህዝቦች ወደ ቀድሞ ሆነታቸው ለመመለስ እንደሚሰሩም ገልፀዋል::

 በሌላ በኩል ባለፈው ቅዳሜ እለት በጎረበት ሶማሊያ ርዕስመዲና ሙቃዲሾ አሸባሪው አልሸባም ባፈነዱት የቦምቢ ጥቃት ውድ ህይወታቸው ላጡ ንፁሃን ዜጎችና ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች በክልሉ መንግስትና ህዝብ ስም የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልፀዋል::

በመጨረሻም የክልሉ ፕሬዝደንት አብዲ መሀሙድ የክልሉ ህዝብ ፀረሰላም ኃይሎችና አሸባሪዎችን በጋራ በመዋጋት ለተገኙን ሰላም በማስጠበቅና ልማትን በማስቀጠል የበኩላቸውን ድርሻ እንድወጡ አሳሲቧል::s