በህገ ወጥ መንገድ ሲጓጓዝ የነበረ ገንዘብ ተያዘ

ጅግጅጋ (Cakaaranews) ሰኞ,ጥቅምት 13 2010,.ም በባቢሌ ከተማ አከባቢ በህገ ወጥ መንገድ ሲጓጓዝ የነበረ አንድ ሚልየን 753 ሺህ 652 የአሜሪካ ዶላር ጨምሮ የተለያየ ሀገራት የመገበያየ ገንዘብ የመያዙን የፌዴራል ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የጅግጅጋ ቅርንጫፍ / ቤት አስታወቀ፡፡

የተያዘው ገንዘብ ከአዲስ አበባ ወደ ቶግውጫሌ በካስተር መኪና ሲጓጓዝ በጥቅምት ሥምንት 2010 ከቀኑ 10 ሰዓት ተኩል በፌዴራል ፖሊስ የኮትሮባንድ ንግድ መከላከል ግብር ሀይል አባላት መያዙን የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የጅግጅጋ ቅርንጫፍ ጽህፈት የህገ ማስከበር ጉዳዮች ምክትል ስራ ኢስኪያጅ አቶ አህመድ መሀመድ ተናግረዋል፡፡

በህገ ወጥ መንገድ ሲጓጓዝ የተያዘው ገንዘብ ውስጥ 1 ሚልየን 753 ሺህ 652 የአሜሪካ ዶላር  580 ሺህ 509 የሰኡዲ ሪያል 32 ሺህ 750 የተባበሩት አረብ ኢሜሪት ድርሃም 1 ሺህ 851 የኮታር ገንዘብ ይገኝበታል፡፡

በህገ ወጥ መንገድ ሲጓጓዝ የተያዙ የመገበያየ ገንዘብ በኢትዮጵያ ብር አሁን ባለው ምንዛሬ 44 ሚልየን 718 ሺህ 091 ብር 30 ሣንቲም ዋጋ ያላቸው ናቸው ብለዋል፡፡

በህግ ወጥ መንገድ የመገበያያ ገንዘቡን ሲያጓጓዙ የተያዙት  ግለሰቦች ጉዳይ በህግ እየተጣራ መሆኑን ምክትል ስራ አስኪያጁ ጨምረው ተናግረዋል፡፡