10ኛው ህዝባዊ ኮንፈራንስ በጅግጅጋ ተጀምሯል

ጅግጅጋ (Cakaaranews) አርቢጥቅምት 17 2010 ዓ›ም .የኢትዮጵያ ሶማ ክልላዊ መንግስትና ህዝብ የጋራ ምክክር መድረክ ክልል መስተዳደር ጽህፈት ቤት ግቢ ካሊ አደራሽ በደማቅ ስነ ስርዓት ተጀምሯል፡፡

በዓመት ሁለት ጊዜ በሚካሄደው በዚሁ የውይይት መድረክ ላይ የክልሉ ፕሬዚዳንት በክቡር አቶ አብዲ መሐሙድ ኡመር የሚመራ ከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች፣ ሀገር ሽማግሌዎች፣ ከ93 ወረዳዎችና ስድሰት ከተማ አስተዳደር የተውጣጡ የኃይማኖት አባቶች፣ሴቶችና ወጣቶች ተወካዮች ተሳታፊ ናቸው፡፡

ለኮንረራሱ ተሳታፊዎች እንኳን ድህና መጣችሁ መልእከት ያስተላለፉት የኢትዮጵያ ሶማሊ ክልል መንግስት ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ አብዲ መሐሙድ ኡመር እንደተናገሩት የጋራ ምክክር መድረኩ ዋና ዓላማ የክልሉን ሠላም፣ ልማትና መልካም አስተዳደር ስራዎች የህዝቡን ተሳትፊነትና ተጠቃሚነት ለማሳድግ ያለመ ነው፡፡

የኮንፈራንሱ ተሳታፊዎች በቆይታቸው ባለፉት ዓመታት በየዘርፉ በህዝብ ባለቤትነት የተመዘገቡ ስኬቶችን ለማስቀጠል ፣ የሽብርተኝነት አመለካከትና ተግባርን አስቀድሙ ለመከላከል የሚያግዙ ሀሳቦች በማንሳት ውይይት እንደሚደረግ ይደረጋል ፡፡

ፕሬዚዳንቱ እንዳሉት በህዝቡና በመንግስት እልህ አስጨራሽ በሆነ መልኩ ባለፉት ዓመታት የተገኘውን ሠላምና ፀጥታ ከአሸባሪ ኃሎች አፍራሽ ተግባር ለመጠበቅ ማህበረሰቡ እንደከዚህ ቀደሙ ከፀጥታ አካላት ጋር የሚያደርጉት ትብብር እንዲያጠናክር ጠይቀዋል፡፡

አሸባሪዎች በቅርቡ በጎረቤት ሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቅዲሾ ውስጥ በንጹሃን ሰዎች ላይ የፈፀሙትን አሰቃቂ አደጋ ከልብ ማዘናቸውን የተናገሩት ፕሬዚዳንቱ ክልሉ ከጎረቤት ሶማሊያ ጋር ሰፊ ድንበር የሚጋራ በመሆኑ አሸባሪዎች ወደ ክልሉ እንዳይገቡ በንቃት መከታተል የሁሉም ኃላፊነት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የክልሉን ህዝብ ከድህነት ለማውጣት የሚያስችል የተፋስስ ወንዞችና ለም መሬት ባለቤት ነው ያለው ፕሬዚዳንቱ የክልሉ መንግስት የህብረሰቡን የስራ ባህል ለማሳድግ ‘ተበዒና ማል’ በሚል ተቋም በማቋቋም ወጣቶች የስራ ክቡርነት እንዲገነዘቡ የሚረዳ የስልጠና ፕሮግራም ተቀርጹ  መተግበር መጀመሩን ገልጸዋል፡፡

ከኦሮሚያ ክልል የተፈናቃሉ ወገኖች መልሶ ለማቋቋም ህዝቡ የጀመረው ድጋፍ ተጠናክሮ የሚቀጥልበት ሁኔታ ሰፊ ውይይት እንደሚካሄድ ይጠበቃል፡፡