የፋይናንስ አስተዳደር ስርዓትን የሚዘረጋበት ስልጠናና ምክክር መድረክ በጅጅጋ ተጀምሯል

ጅግጅጋ(Cakaaranews)ኅዳር 7/ 2010ዓ.ም.የኢ.ሶ.ክ.መ. የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የሂሳብ አያያዝ ስርዓት ለማስፋፋትና ለማማከር በፋይናንስ አስተዳደር ስርዓት ዙሪያአሰራርን የሚያሳለጥ ስልጠና አዘጋጅቷል

 

 ይህ የአቅም ግንባታ ስልጠና የተዘጋጀው የክልሉ የፋይናንስ አስተዳደር ሥርዓት፤ተዛማጅ ደንቦችና መመሪያዎችን የተሻለ ክህሎት ለመፍጠር ሲሆን በመድረኩ ላይም  የዞኖችና ወረዳዎች ፋይናንስ እና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊዎችእና የወረዳ አስተዳዳሪዎችም በቀርያ ዶዳን መሰብሰቢያ አዳራሽ ተሳትፏል።

በተጨማሪም የኢ.ሶ.ክ.መ. የፋይናንስ እና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ አህመድ አብዲ መሀመድ በበኩላቸው የስልጠናው አላማ የፋይናንስ አስተዳደር ስርዓት ማሻሻያ
((PFM)እና ህዝብ መሰረት የፋይናንስ አገልግሎት ፕሮግራምን(PBS) በክልሉ እና በወረዳ ደረጃ ከሚገኙ አካላትጋር ውይይት ለማድረግ ነው ብሏል።


በመጨረሻም ሰልጣኞቹ  ወደ
ሥራ ቦታዎቻቸው ከተመለሱ በኋላ ከዚህ ስልጠና የቀሰሙት ልምድን በውጤታማ መልኩ ትግባራዊ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል ብሏል ሃላፊው።