አዲስ የኢትዮጵያ ሶማሌ ተፈናቃዮች ወደ ጅግጅጋ እየገቡ ነው!

ጅግጅጋ (cakaaranews)ቅዳሜ ህዳር 09/2010ዓ.ም. የኢ.ፈ.ዴ.ሪ.መንግስት የኢትዮጵያ ሶማሌና የኦሮሚያ ክልል ግጭቶችን በሚያስቆሙበትና በሁለቱ ክልሎች መካከል ዘላቂ ሰላም ለመምጣት በጋራ የሚሰራበት ወቅት፤ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በአሮሚያ ክልል የሚኖሩ የኢትዮጵያ ሶማሌ ተወላጆች እንደ-አዲስ እያፈናቀሉ ይገኛሉ።

በአሮሚያ ክልል ምዕራብ ሐረርጌ ዞን በበልበሌቲና በመኤሶ አከባቢዎች እንድሁም በምስራቅ ሐረርጌ ዞን በጉርሱም ወረዳ አከባቢ ከጥንት ጀምሮ ሲሚኖሩ የቆዩት የኢትዮጵያ ሶማሌ ተወላጆች ከቤት ንብረታቸውና ከቄያቸው ከህዳር 6 ቀን፤2010ዓ.ም. ጀምሮ እያፈናቀሉ ይገኛሉ።በተጨማሪም የኢትዮጵያ ሶማሊ ክልላዊ መንግስት በአዲስ መልኪ ከኦሮሚያ የተፈናቀሉ ወገኖች በቆለቺ ቀበሌ በሁለት መጠሊያ ጣቢያዎች የመልሶ ማቋቋም ስራ እያከናወነ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት በሮ እንደአዲስ ከኦሮሚያ የተፈናቀሉት የኢትዮጵያ ሶማሌ ተፈናቃይ ወገኖቹ ከ300 አባ-እማወራዎች በላይ መሆናቸውና ከለበሱት አልባሳት በስተቀር ከንብረታቸውና ሀብታቸው መፈናቀላቸውን ገልፀዋል።

በመጨረሻም  የኢትዮጵያ ሶማሊ ክልላዊ መንግስት በአዲስ መልኪ ከኦሮሚያ የተፈናቀሉ ወገኖች በርካታ የምግብ፤የመድሃኒት፤የቤት ቁሳቁሶች፤የአልባሳትና የመጠለያ ድጋፍ እያደረገለቸው ይገኛል።