የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት 4000 ወጣቶች በእጣ ቀጥሯል

ጅግጅጋ(cakaaranews) ማክሰኞ፤ህዳር 12/2010ዓ.ም.የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት የወጣቶች ስራ አጥነት ለመቀነስና ለተገልጋዩ ህዝብ በአግባቡ ለማገልገል ከሀገሪቱ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተመረቁ የክልሉ ሥራ አጤ ወጣቶች በሙያቸው እንድያገለግሉ በእጣ ተቀጥሯል።

በተጨማሪ በዛሬ እለት በጅግጅጋ በሰይድ መሀመድ አደራሽ በተለያየ የሀገራችን ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፤በተለያዩ የትምርት ዘርፎች የተመረቁት ከ4000 በላይ የክልሉ ሥራ አጤ ወጣቶች የተመደቡበት የስራ ቦታና የሥራ መደቡ የተገለጸበት የእጣ ወርቀት በማንሳት እራሳቸው በራሳቸው እጅ እንድቀጠሩ ተደርጓል።

በምዳባ ሥነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙትና ለአዳዲስ ሰረተኞችን መልዕክታቸው ያስተላለፉት የክልሉ ም/ፕሬዝዳንትና የግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሱኣድ አህመድ ፋረህ ናቸው በመቀጠሊም ባለፈው አመት የክልሉ መንግስት ከአገሪቱ ዩኒቬርሲቲዎች የተመረቁት 7000 ወጣቶችን በእንደዚህ አይነትበእጣ መቀጠራቸውና በርካታ አመርቂ ሥራዎች ማከናወናቸው የሚታወስ ሲሆን አዳዲስ ሰረተኞችሁ በተመደቡበት አከባቢዎች ለሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች በቅንነትና በሃላፊነት እንድያገለግሉ ጥሪያቸውን አቀርቧል።

በተመሳሳትም የክልሉ መስተዳደር ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አብድመሀድ መሀመድ አባስ በበኩሉ በእጣ በራሳቸው እጅና በእድላቸው የተቀጠሩት አዲስ ምሩቃን ሰረተኞቹ እድላቸው በመደበበት አከባቢ እንድሄዱና በእውቀታቸው ለተጋልጋዩ ህዝብ በተታሪነትና በቅንነት እንድያገለግሉ ጠይቋል።

በሌላበኩል የክልሉ ሲቪል ሴርቪስና ሰው ኃይል ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አህመድ ኮሬ በበኩላቸው መንግስት የሚያከናወናቸው የልማት እቅዶች ተግባራዊ ለማድረግ በዘርፉ የተማረ ሰው ሃይልሚና ከፍተኛ ነው ብሏል።በተጨማሪም ከሀገሩቱ ዩኒቬርሲቲዎች የተመቀሩ የክልሉ ተወላጅ ተማሪዎች ሁሉም የክልሉ መንግስት በዘር፤በቋንቋና በእምነት ሳይለዩ በተመረቁበት የሙያ አይነት እንደምመደብ አክሎ አዲስ ተቀጣሪዎቹ ለህዝቡ ቀልጣፋ አገልግሎት እንድሰጡ ጠይቋል።

በመጨረሻም በእጣ የተቀጠሩት ተማሪዎችሁ በእጣ ማንሳት መቀጠራቸው እጅግ በጣም ደስተኛ ከመሆናቸው ባሻገር በእጣ መሰረት ያደረገ የሰረተኞች ምደባ መርሃግብሩ በጣም ፊትሃዊ መሆኑ፤እና ከዘመድ አድሎና ከትውውቅ የፀዳ ሥርዓት መሆኑን ገልፀዋል።