የ2010 ባጀት አመት በልዩ ድጋፍ የሚሹ ክልሎች እቅድ አፈጻጸም የሚገመገምበት የጋራ ምክክር መድረክ በጅግጅጋ ከተማ ተካሄዷል

ጅግጅጋ(Cakaaranews)ሀሙስ ህዳር 22/2010.የኢ.ፈ.ዴ.ሪ.የፈዴራለና አርቢቶአደር ልማት ጉዳዮች ሚንስተር የልዩ ድጋፍ የሚሹ ክልሎች የ2009ዓ.ም.እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት የሚግመግመበትና የ2010እቅድ  የሚመከርበት መድረክ በጅግጅጋ ከተማ በካሊ2 አደራሽ ተካሄዷል።በመድረኩ ላይም የፈዴራልና አርቢቶደሮች ልማት ጉዳዮች ሚንስተሪ ሚንስተር አቶ ከበደ ጫነ፤በአሜሪካ የኢትዮጵያ ባለሙስልጣን አምባሳደር ካሳ ተክለብርሃን፤የሚንተር መ/ቤቱ ሚንስተር ዴታና ሌሎች የሥራ ሃላፊዎችና የክልሉ መንግስት ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች የክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ አብዲ መሀሙድን  ጨምሮ ተገኝቷል።

በመድረኩ መክፈችያ ላይ ንግግር የደረጉት የክልሉ ፕዳንት ክቡር አቶ አብዲ መሀሙድ ኡመር ክልሉ በ2009ዓመት ያከናወናቸው ሰፊ  የልማት ሥራዎች በማቅረብና የፈዴራልና አርቢቶደሮች ልማት ጉዳዮች ሚንስተሪ ለክልሉ አርቢቶአደር ማህበሰብ ላደረጉት ልዩ ድጋፍ የላቀ ምስጋና በማቅረብ፤የመድረኩ ዋና አላማ የ2009 እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ደካማና ጠንካራ ጎኖችን ለመገምገምና የ2010ባጄት አመት እቅድ፤ስተራቴጅዎችና አቅጣጫዎችን በጋራ ለመመካከር እንደሆነ ተናግሯል ፕሬዝዳንቱ።

በሌላ በኩል የፈዴራልና አርቢአደር ልማት ጉዳዮች ሚንስተሪ ሚንስተር አቶ ከበደ ጫነ በበኩሉ የመድረኩ አስፈላጊነት በ2009ዓ.ም.ክልሉ መንግስትና ሚንስተር መስሪያቤቱ በክልሉ በጋራ ያከናወኑት የአርቢቶአደር ለማት ሥራዎች በጋራ በመግምገም ክፍተቶችን፤ጠንካራ ጎኖችና ምርጥ ተመክሮችን ለመየትና የ2010 ባጀት አመት የልዩ እቅዶቻችን ለመጣጣምና አቅጣጫዎች ለማስቀመጥ ወሳኝ ነው ብሏል።ተጨማሪም መድረኩ በተለያዩ ምክንያቶች የዘገየ እንደሆነና የ2010 አንደኛ ሩቡ አመት የተከናወኑ ስራዎች በሪፖርቱ እንደተካተተና ሚንስተር መ/ቤቱና ክልሉ መንግስት በዘንዲሮ አመት በአርቢቶአደር ልማት እቅዱ በዋነኝነት በአዳዲስ የመንደር መሰባሰብ ስራዎችና በመስኖ እርሻዎች ዙሪያ ትኩረት እንደሚሰጡ ገልጿል ሚንስተሩ።

በተመሳሳይም በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ካሳ ተክለ ብርሃን በበኩላቸው የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ፈጣን ልማት በርካታ ውጣ ውረዶች ያሳለፈና የመጸዋት የተከፈለበት እንደሆና የክልሉ ልማት ስራዎች ታሪክ ቢጻፍ የማያቁና ሰፊ እንደሆነም ተናግሯል።የክልሉ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎቹ አበረታች መሆናቸውም ገልጿል አምባሳደር ከሳ።በመቀጠሊም ድሮ ክልሉ የራሱን ስራ ብቻ የሚትኮር ክልል እንደነበረና አሁን ግን የሀገሪቷ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎች በሰፊው እየተሳተፈ ያለውና ድምጹን ጆሮ መስጠት ያለበት ክልል ነው ብሏል። በክልሉ በርካታ የጸጥታ የመስረተ ልማት፤የጎረቤት አጋራት ድንበር ጥበቃ ስራዎች እየሰራ ያለው ክልል መሆኑንም ጠቅሷል አምባሳደሩ።በአጭር ጊዜ የተገኘው የክልሉ አመርቂ የልማት ስራዎች ጎንለጎን የሚሄዱት ደህነትና ኋላቀርነት እንቅፋቶች ለማጥፋትም በርካታ የአስተዳደር ጥረቶች እንደሚጠይቅና  ደግሞ ማስመሰል ሳይሆን ከልቤና የምር ያመንኩት ብሏል አምባሳደር ካሳ ተክለብሃን።ይህ ደግሞ በክልሉ እየተመራ ያለውና በመልካም አስተዳደር የተላበሱ አመራሮች የተገኙ መልካም ሥራዎች ናቸው ብሏል።በክልሉ ብዙ አመራሮች እየተለዋወጡና ሁሉም የክልሉ ልማት ስራዎች በስኬት ሳያጠናቀቁ በሆነ ቦታ ላይ ማስቆማቸው በመጠቀስ፤የአሁኑ የአመራር ግን በርካታ የልማት እንቅፋቶችና አስከፊ ችግሮችን ችላ ሳይሉ የቻሉና የታገሱ አመራር መሆናቸው አክሎ ለወደ ፊትም ጠንኪሮ መቀጠል እንዳለባቸውም አሳስቧል።ወደ ክልሉ የመጠሁበት ዋና ዋና አላማ አንደኛው አዲሱ ሚንስተር አቶ ከበደ ጫነ ለማስተዋወቅና ከክልሉ ባላድርሻ አካላት ጋር ለማስተሳሰር ሲሆን ሁለተኛው ወደ አዲሱ ስራያ ስለሚሄድ “ቻው” ብዬ ለመሄድ ነው። በአሜሪካ የሚገኙ የኢት-ሶማሌ ኮሙኒቲ በአገራችን ልማት ትልቅ ድጋፍ ያደረጉና በተላይም በህዳሴ ግድባችን ለሚደረጊለት ድጋፍ ከፍተኛ ሚና የተጫወቱ በመሆናቸውና ከኔ ጋርም የበለጠ እንደሚያጠናከሩ እምነት አለኝ ሲሉ ተናግሯል።

በመጨረሻም በክልሉ በ2009ዓ.ም. የከፊል አርቢቶ አደር አከባቢዎችና የመንደር ማሰባሰብ ስራዎች ሪፖርት በፈዴራልና አርቢቶአደር ልማት ሚንስተሪ ሚንተር ዴታ ቀርቧል።በዚህ ረገድ የፈዴራልና አርቢቶአደር ልማት ሚንስተር በ2009 በክልሉ 6917እማ/አባወራዎች በመንደር እንድሰባሰብ ተቅዶ 6825 እማ/አባወራዎች በመንደር እንድሰባሰብ ተችሏል፤በተመሳሳይም በላፎ አመት በተከሰተው ኢሊኖ ምክንያት ከመንደራቸው ያራቁ 1774 እማ/አባወራዎች ወደ መንደራቸው ለመመለስ ታቅዶ ሙሉ በሙሉ ተሳክቷል።እንድሁም በመንደር የተሰባሰቡ እማ/አባወራዎች ሁሉም የመስረተልማት ስራዎች እንደ የትምህርት አገልግሎት፤የጤና አገልግሎት፤የዉሃ አገልግሎትና የማህበራዊ ጉዳዮች እንደተሞላለትና እንድሁም ዘመናዊ የእንስሳት እርባታ፤ዘመናዊ የእንስሳት መኖ አመራረትና የመስኖ እርሻ ስራዎችም መከናወናቸውን በሪፖርቱ ተመልክቷል።