የኢ.ሶ.ክ.መ.ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አብዲ መሀሙድ የውጭ ባለሀብቶች ልዑካን ቡዱን በጽ/ቤቻው ተቀብሎ አነጋገሩ

ጅግጅጋ(Cakaaranews)ሀሙስ ህዳር 22/2010. የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት ከፍተኛ ባላስልጣናት  የአውስተረሊያ ባላሀብቶችና በኑዩዚላንድ የሚኖሩ የክልሉ ተወላጅ ዲያስፖራ አባላት ልዑካን ቡዱን  በጅግጅጋ የጋራድ ዊልዋል አለማቀፍ ኣየር ማርፊያ ደማቅ አቀባበል አደርጎላቿል

የክልሉ ም/ፕሬዝዳንትና የግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ሱኣድ አህመድን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ ባላስልጣናት ልዑካን ቡዱኑ ደማቅ አቀባበል ካደረጉላቸው በኋላ  የክልሉ ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አብዲ መሀሙድ ኡመር ከክልሉ ካቢኔ አባላት ጋር በመሆን ልዑካን ቡዱኑ በጽ/ቤታቸው ተቀብሎ አነጋገሩ።

በውይይቱ መፍችያ ላይም የክልሉ ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አብዲ መሀሙድ  ክልሉን ኢንቬስት ለማድረግ የመጡ የውጭ ባላሀብቶች የላቀ ምስጋና በማቅረብ፤ክልሉ ለኢንቬስትመንት ምቹ መሆኑና  የክልሉ ጸጋ የተፈጥሮ ሀብትና የክልሉ አጠቃላይ ሆነታ የሚዳሰስ ሪፓርት አቀርቧል።በተጨማሪም በክልሉ የሚገኙ ኢቬስትመንት እድሎች መዋእለነዋያቸው የሚያፈሰሱ የወጭ ባላሀብቶች የክልሉ መንግስት አስፈላጊ ግብዓት ሁሉ እንደሚያሟላቸውና ክልሉ ለማንኛውም ባላሀብት ክፍት መሆኑን ፕሬዝዳንቱ ገልጿል።

በሌላ በኩል ልዑካን ቡዱኑ ጅግጅጋ ዩኒቬርሲቲ በጎበኙበት ወቅት የጅግጅጋ ዩኒቬርሲቲ የአዳሚና ምርምር ም/ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ኢልያስ ኡመር የዩኒቬርሲቲ የመማር ማስተማር ህደትና በዩኒቬርሲቲ ስለሚማሩ ተማሪዎች ብዛትና ዩኒቬርሲቲው አገልግሎት ከሚሰጡ ዲፓርትመንቶች የሚዳሰስ አጭር ርፖርት አቀርቧል።በተጨማሪም ልዑካን ቡዱኑ የጅግጅጋ መለስ ዜናዊ ሪፊራል ሆስፒታል በጎበኙበት ወቅትም ሆስፒታሉ ለህብረተሰቡ ስለሚሰጠው አገልግሎትና በሆስፒታሉ ስለሚገኙ ዘመናዊ መሳሪያዎች አጠቃቀም ዙሪያም የሆስፒታሉ የሥራ ሃላፊዎች አስፈላጊው መረጃ ሰጥቷል።