የኢ.ሶ. ህ.ዴ.ፓ ከፍተኛ አመራርና የክልሉ ካቢኔ አባላት የተፈናቃዮች መልሶ ማቋቋም ውሰነ አሳልፏል

ጅግጅጋ(Cakaaranews)ቅደሜ፤ህዳር 23 ቀን 2010.የኢትዮጵያ ሶማሊ ህዝብ ዴሞክራሲ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሩና የክልሉ ካቢኔ አባላት የክልሉ ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አብዲ መሀሙድ ኡመርና የኢ.ሶ. ህ.ዴ.ፓ ሊቃመንበር አቶ መሀመድ ረሺድ ኢሳቅን ጨምሮ ከኢትዮጵያ ሶማሌና ከኦሮሚያ ክልሎች የተፈናቀሉ ወገኖች ወደ ቄያቸው የሚመለሱ ዉሳነ አሳልፏል። 

የኢትዮጵያ ሶማሊ ህዝብ ዴሞክራሲ ፓርቲ ከፍተኛ አመራርና የክልሉ ካቢኔ አባላት ዛሬ ባካሄዱት ስብሰባ ከኦሮሚያ ክልል የተፈናቀሉ የሶማሌ ወገኖች በራሱ በክልሉ መንግስት ወደ ቄያቸው የማስመለስ ሥራ ከወዲሁ እንደሚጀመርና ከሶማሌ ክልል የተፈናቀሉ ኦሮሞ ወንድማሞች በተላይ በጅግጅጋና በሌሌች አከባቢዎች በተለያዩ ንግድ ሥራዎች ተሰማርቶ የነበሩ የኦሮሞ ወንድማሞች ወደ ክልሉ የሚመለሱበት ስራ እንደሚሰራና ኦሮሞ ወገኖቹ ወደ ክልሉ በሚመጡበት ጊዜ ደማቅ የወንድማሚነት አቀባበል እንደሚደረግለቸው ክልሉ አስታውቋል።ይህ ደግሞ ሁሉም የኢትዮጵያ ዜጎች በአገራቸው በፈለጉት አከባቢ  ለመኖር እኩል ህገመስግስታዊ መብት ስለላቸው ነው ብሏል የክልሉ መንግስት።

መጨረሻም የክልሉ ህዝብ፤የክልሉ መሪ ድርጅት ኢ.ሶ. ህ.ዴ.ፓና የክልሉ መንግስትምከክልሉ የተፈናቀሉ ኦሮሞ ወንድመቻችን በተላይ በተለያዩ ንግድ ሥራዎች ላይ ተሰማርቶ የነበሩ የኦሮሞ ወገኖች  ወደ ቄያቸው እንድመለሱ ጥሪ አቀርቧል ።