12ኛው የቤሔር፤ቤሔረሰቦችና ህዝቦች በዓል ቀን በአገር አቃፍ ደረጃ በሰመራ ከተማ ተከብሯል

ሰመራ(Cakaaranews)አርቢ ህዳር 29/2010. 12ኛው የአትዮጵያ ቤሔር፤ቤሔረሰቦችና ህዝቦች በዓል ቀን በአገር አቃፍ ደረጃ በአፈር ክልል ርዕስመዲና በሰመራ ከተማ በደመቀ ሆኔታ  ተከብሯል።

በኢትዮጵያ ህዝቦች ቀልቢ አንድነትና ክብር የሚቸረው 12ኛው የአትዮጵያ ቤሔር፤ቤሔረሰቦችና ህዝቦች ክብረ በዓል 29 ቀን በአገር አቃፍ ደረጃ በአፈር ክልል  በሰመራ ተከብሯል። በክብረ በዓሉ ላይ ከፍተኛ የኢ.ፈ.ዴ.ሪ.መንግስት ባላስልጣናት የኢ.ፈ.ዴ.ሪ.ጠቅላይ ሚንስተር አቶ ኃ/ማርየም ደሳለኝ፤ የክልሎች ርዕሳን መስተዳደሮች ክቡር አቶ አብዲ መሀሙድ ኡመርን  ጨምሮየኢ.ፈ.ዴ.ሪ.የፈዴሬሽን ም/ቤት አፈጉባኤ አቶ ያለው አባተ ተገኝቷል።በተጨማሪም የጎረቤት አገራት መሪዎች እንደ የሱዳን ፕሬዝዳንት ኡመር ሀሰን አልበሺር፤የጀቡቲ ፕሬዝዳንት እስማኢል ኡመር ጌሌና የሶማሊያ ም/ጠቅላይ ሚንስተር ማህዲ አህመድ ጉሌድ እና ሌሎች የአለማቀፍ ክቡር እንግዶችም በበዓሉ ታድሟል።

 በበዓሉ ላይ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም የሃገሪቱ ህዝቦች መተሳሰብና መከባበር ትልቁ ብሄራዊ ሃብት መሆኑን ተናግረዋል። ዕለቱ ሃገሪቱን ከመበታተን አደጋ የታደገና ለኢትዮጵያውያን ልዩ ትርጉም ያለው ህገ መንግስት የፀደቀበት መሆኑን ገልጸዋል።ዕለቱ በህዝቦች መፈቃቀድ ላይ የተመሰረተ አንድ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ማህበረሰብ ለመፍጠር ጉዞ የተጀመረበት መሆኑን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ የሃገሪቱ ህዝቦች የስልጣን ባለቤትነት የተረጋገጠበት መሆኑንም ገልጸዋል።በዓሉ የጋራ መግባባትና ዕኩልነት የህዝቦች መለያ እንዲሆን ቃል ቢገባም፥ አንዳንድ አክራሪ፣ ጠብባና ትምክህተኛ ሃይሎች ይህን የህዝቦች መለያ ለማጠልሸት መንቀሳቀሳቸውን አንስተዋል።በተጨማሪም መንግስትም በፅኑ መሰረት ላይ የቆመውን የህዝቦችን አንድነትና እኩልነት ለመናድ የሚንቀሳቀሱ አክራሪ ሃይሎችን እንቅስቃሴ ለመግታት እየሰራ ነው ብለዋል።አሁን ላይ የህዝቦችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥና ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍል እንዲኖር እየተሰራ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስት።መንግስትም በማህበራዊ መስክ በተለይም የወጣቱን ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ አንጻር ያለውን እድል አሟጦ ለመጠቀም እንደሚሰራ አስረድተዋል።

የኢ.ፈ.ዴ.ሪ. የፈዴሬሽን ምክርቤት አፈጉባኤ አቶ ያለው አባተ የቤሔር፤ቤሔረሰቦችና ህዝቦች በዓል ቀን የኢትዮጵያህዝቦች  እኩልነት፣ ፍቅርና አንድነትም የኢትዮጵያ ህዝቦች መለያ ናት ብሏል።በመቀጠሊም   በዓሉ ኢትዮጵያ ህዝቦች የሀገራቸውን የህዳሴ ለውጥ ያረጋገጡበት ቀን  መሆኑን አስረድቷል ።የቤሔር፤ቤሔረሰቦችና ህዝቦች በሔራዊ ቃልኪዳን የሆነው ህገመንግስታችንና የፌደራሊዝም ሥርዓታችን በፍቅርና አንድነት አጠናቅሮ እንድቀጥሉም  አፈጉባኤ ያለው አባተ አሳስቧል።

 በበዓሉ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የሱዳኑ ፕሬዚዳንት ኦመር ሀሰን አልበሽር፥ ዕለቱ የሁለቱን ሃገራት ህዝቦች ግንኙነት የምናድስበት ነው በማለት ንግግር አድርገዋል።የኢትዮጵያ ህዳሴ የሱዳን ህዳሴ ነው ያሉት ፕሬዚዳንቱ፥ ከዚህ አንጻርም ለኢኮኖሚ ውህደት የሚረዱ ትልልቅ ፕሮጀክቶችን በጋራ እንሰራለን ብለዋል።የጂቡቲው ፕሬዚዳንት እስማኤል ኦማር ጌሌህ በበኩላቸው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈው፥ ዕለቱ የኢትዮጵያ ህዝቦችን አንድነትና ብዝሃነት አመላካች መሆኑን ጠቁመዋል።የሶማሊያው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር  ማህዲ አህመድ ጉሌድ ንግግር ያደረጉ ሲሆን፥ የበዓሉ መከበር በኢትዮጵያ ህዝቦች መካከል ያለውን ሰላም፣ አንድነትና መቻቻል ማሳያ መሆኑን ነው የተናገሩት።የኢፌዴሪ ህገ መንግስትም ህዝቦች በአንድነት ልዩነቶቻቸውን እንዲፈቱ ያስቻለና የቡድንና የግለሰብ መብቶችን ያስከበረ መሆኑንም ገልጸዋል።

በበዓሉ ሥነ-ስርዓት መገባደደያ ላይ የክልሎች ርዕሳንመስተዳደሮችና በበዓሉ የተጋበዙ የምስራቅ አፍሪካ መሪዎችና ሎሌች ክቡር እንግዶች በጠቅላይ ሚንስተሩ የተለያዩ ሽልማቶች ተበርኪቶላቿል።በተጨማሪም የኢትየጵያ ሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አብዲ መሀሙድ  ኡመር ከሽልማቱ ባለፈ የህዳሴ ግድብ ተዘዋዋሪ ዋንጫ ተረክቧል።