የኢ.ሶ.ክ.መ.ፕሬዝዳንት አቶ አብዲ መሀሙድ በ12ኛው ቤሔር፤ቤሔረሰቦችና ህዝቦች ክብረ በዓል ላይ የህዳሴ ግድብ ዋንጫ ተረክቦ ወሳኝ ንግግር አደረጉ

ሰመራ(cakaaranews)አርቢ ህዳር 29/2010 የኢ.ሶ.ክ.መ.ፕሬዝዳንት በቤሔራዊ ደረጃ በአፈር ክልል ርዕስ-መዲና በሰመራ ከተማ  በደማቅ ሆኔታ የተካሄደው  12ኛው የኢትዮጵያ ቤሔር፤ቤሔረሰቦችና ህዝቦች ክብረ በዓል ላይ ከኢ.ፈ.ዴ.ሪ.ጠቅላይ ሚንስትር ክቡር አቶ ኃይሌማርየም ደሳለኝ የተላቁ ህዳሴ ግድብ  ዋንጫ ተረክቦ ወሳኝ ንግግር አደርጓል።

የኢ.ሶ.ክ.መ.ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አብዲ መሀሙድ ኡመር የታላቁ ህዳሴ ግድባችን ተዘዋዋሪ ዋንጫ መረካባቸውን ደስተኛ መሆናቸውና ክልሉ የተጣለበት ሃላፊነት በአግባቡ እንደሚወጡና ከፍተኛ ገቢ እንደሚያስገኝም ገልጿል።

በመጨረሻም  ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዋንጫ አገሪቷ ከሃይል ማመንጨት የሚታገኘው ኦኮኖሚያዊ ፋይዳ ባሻገር የኢትዮጵያ ቤሔር፤ቤሔረሰቦችና ህዝቦች አንድነትና መቻቻል ያጠናክራል ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ።በተጨማሪም ህገ-መንግስታችን እና የፈዴራሊዝም ስርዓቱ ያረጋገጠው የህዝቦች አንድነትና እኩልነትን ለማጠናከርና ማስተሳሰርን የጎላ ጥቅም እንዳለውም ጠቆሟል።