በፋይናንስ አሰራርና የባጄት አጠቃቀም የሚታርሚበት ምክክር መድረክ በጅግጅጋ ከተማ ተጀመረ

ጅግጅጋ (cakaaranews)ማክሰኞ ታህሳስ 3/2010. በኢ.ሶ.ክ.መ. ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ አዘጋጅነት የፋይናንስ አሰራር መመሪያዎችና የባጄት አጠቃቀም ስህተቶችን የሚታርሚበት ምክክር መድረክ በጅግጅጋ ከተማ ተካሄዷል።

በምክክር መድረኩ ላይ ንግግር የደረጉትየክልሉ የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ም/ኃላፊ አቶ ጀማል ፋራህ ወርሞጌ የመድረኩ አላማ የፋይናንስ አጠቃቀምና የውስጥ ኦዲት አሰራርን የሚጠናከርበት ነው ብሏል።ያለን የፋይናንስ ሀብት የፋይናንስ መመሪያዎች ተክትሎ መቀጠም ግዴታ መሆኑን ነው ሃላፊው የገለጹት።በተጨማሪም በየሩዕ አመቱ በፋይናንስ አጠቃቀም ዙሪያ ያጋጠሙ ችግሮችና መፍትሄዎችን ከባላሙያዎችና ከባላድርሻ አካላት ጋር በቋሚነት የሚገመገምበትና የሚታረሚበት መድረክ ነው ብሏል ም/ኃላፊው።

በመጨረሻ ይህ በክልሉ መ.ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ አደራሽ በፋይናንስ አሰራርና ባጄት አጠቃቀም ዙሪያ እየተካሄደ ያለው መድረክ የፋይናንስ ውጤታማ አሰራሮች እንደሚወጡና የባጄት አጠቃቀም ስህተቶችን ይታረማሉ ተብሎ ይበቃል።