በኢ.ሶ.ክ.መ.ምክትል ፕሬዝዳንትና የከተማ ልማትና ኮንስተረክሽን ቢሮ ኃላፊ የሚመራ የክልሉ ከፍተኛ ልዑካን ቡዱን ወደ ሶማሊላንድ አመሩ

ሀርገይሳ(cakaaranews)ማክሰኞ፤ታህሳስ 3/2010ዓ.ም. በኢ.ሶ.ክ.መ. ም/ፕሬዝዳንትና የከተማ ልማትና ኮንስተረክሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዲሀኪም ኢጋል የሚመራ የክልሉ ከፍተኛ ልዑካን ቡዱን የሶማሊላንድ አዲሱ ፕሬዝዳንት አቶ ሙሴ ቢሂ የሹመት ሥነ-ስርዓት ለመሳተፍ ወደ ሶማሊላንድ አቀኑ።ልዑካን ቡዱኑ በድንበር ከተሟ ቶግወቻሌ በደረሱበት ወቅት በሶማሊላንድ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚንስተር ያሲን ሞሀሙድ የሚመራ ከፍተኛ የመንግስት ልዑካን ቡዱን ከቶግወጫሌ ነዋሪዎች ጋር  ደማቅ አቀባበል አደርጎላቿል።

በአቀባበል ሥነስርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ ሶማሊ ክልል ም/ፕሬዝዳንትና የከተማ ልማትና ኮንስተረክሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዲሀኪም ኢጋል ኡመር ለሚዲያ ባደረጉት ንግግር በሶማሊላንድ መንግስት የተደረገላቸው ደማቅ የጎረቤት ወደጅነት አቀባበል በጣም እንደተደሰቱበት ገልጿል። የጉዞ አለማቸውም በቅርቡ በሶማሊላንድ የተካሄደው የፕሬዝዳንትነት ምርጫ ያሸነፉት ፕሬዝዳንት ለሚደረግለት የሹመት ሥነስርዓት ለመገኘት ነው ብሏል ።በተጨማሪም  ም/ፕሬዝዳንቱ አቶ አብዲሀኪም በኢትዮጵያና ሶማሊላንድ በዲብለማሲ፤በንግድና በጸጥታ፤በአለማቀፍ ትብብርና በመልካም ጉርቢትና ዙሪያ ያለው የላቀ ግንኙነትና ወዳጅነት የበለጠ ለማጠናከር ነው ብሏል።

በሌላ በኩል የሶማሊላንድ የአገር ውስጥ ሚንስተር አቶ ያሲን መሀሙድ ከኢትዮጵያ ሶማሊ ክልል የመጡ ልዑካን ቡዱን መምጣታቸውና በሶማሊላንድ መንግስት የተደረግላቸው አቀባበል ከመደሰታቸው ባሻጋር ለአዲሱ የሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት ለሚደረግለት የሹመት ስነ-ሥርዓት  የክልሉ መንግስት ልዑካኑ በኢትዮጵያና ሶማሊላንድ መካከል ያለው መልካም ግንኙነትን ያጠናክራል ብሏል።