የኢ.ፈ.ዴ.ሪ.የፈዴራልና የክልል ከፍተኛ ልዑካን ቡዱን የአዲሱ ሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት የሹመት ቃለመሀላ ስርዓት ተካፈሏል

ሀርጌይሳ (Cakaaranews) እሮብ፤ታህሳስ 4ቀን/2010.በኢ.ፈ.ዴ.ሪ. የትራንስፖርቲ ሚንስተሪ ሚንስቴር ክቡር አቶ አህመድ ሺዴ የሚመራ.የፈዴራል ልዑካን ቡዱን እና  በኢ.ሶ.ክ.መ.ምክትል ፕሬዝዳንትና የከተማ ልማትና ኮንስተረክሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ አብድሀኪም ኢጋል የሚመራ የክልል ልዑካን ቡዱን ከክልሉ የሀገር ሽማግሌዎች ሊቃውንት ጋር በመሆንበዛሬ እለት በሶማሊላንድ ርዕስ-መዲና በሀርጌይሳ ከተማ የተካሄደውን የአዲሱ ሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት አቶ ሙሴ ቢሂ የስልጣት ሹመት ቃለመሀላ ሥነ-ስርዓት ላይ ተካፍሏል። በሥነስርዓቱ ላይ የዲጀቡቲ፤ኬንያ፤የዩጋንዳና ሌሎች የጎረቤት አገራትና  እንድሁም የአውሮፓ ህብረትና ሌሎች የ ልዑካን ቡዱኖች ተገኝቷል።

በሌላ በኩል  የኢ.ፈ.ዴ.ሪ. ትራንስፖርቲ ሚንስቴር አቶ አህመድ ሺዴ ለሶማሊላንድ ህዝብ ከኢ.ፈ.ዴ.ሪ. ጠቅላይ ሚንስቴር ክቡር አቶ ኃይለማርየም ደሳለኝ የተላክላቸው የእንኳን ደሳላችሁ መልዕክታቸው አስተላልፏል።በተጨማሪም የኢ.ፈ.ዴ.ሪ. ሚንስቴሩ አቶ አህመድ ሺዴ በንግግራቸው በኢትዮጵያና ሶማሊላንድ መካከል ያለው ታሪካዊ የዲብለማሲ፤የንግድ ትስስርና በቀጠናው የሰላምና የጸጥታ ግንኙነትን አብራርቷል።ለአዲሱ ፕሬዝዳንት የእንኳን ደስላቹ መልዕክታቸው ከማስተላለፉ ባሻገር በኢትዮጵያና ሶማሊላንድ መካከል የነበረውን ዘርፈ-ብዙ የመልካም ጉርቢትና ትብብርን ማጠናከር እንዳለበትም ሚንስቴሩ ጠቆሟል።

ይህ በደማቅ ሁኔታና በአማረ መልኩ የተዘጋጀው የሹመት ቃለ-መሃላ ስነ-ስርዓት ላይ በዛሬው ዕለት ስልጣናቸዉን ያስረከቡት የቀድሞ የሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት ክቡር አህመድ መሀመድ ሲላንኞ በበኩላቸው ረጅም ንግግር  በማድረግ ለአዲሱ ፕሬዜዳንት በሶማሊላንድ የተጀመረዉን የልማት ጉዞ ቀጣይነት እንዲያስቀጥሉና ውጤታማነቱን ያረጋገጠ ልማትን በማስቀጠል እንዲሁም ልማቱ የተቀመጠዉን ግብ የመታና የሶማሊላንድን ህዝብ ረዕይን ያሰካ እንዲሆን  አደራ በመስጠት መልዕካታቸዉን አስተላልፏል፡፡ 

ይህ በእንዲህ እንዳለ ሆኖ ስልጣኑን የተረከቡት አዲሱ ፕሬዜዳንት ክቡር አቶ ሙሴ ብሂ አብዲ በመጀመሪያ በስነ-ስርዓቱ ላይ ከተለያዩ ጎረቤት ሀገራት የታደሙትንና የተገኙት እንግዶቻቸዉን በማመስገን፣ የተረከበዉን ሀላፊነት ለህዝቡ ፍትሃዊ በሆነ መልኩ እንደሚያገለግሉላቸው ቃል በመግባት እንዲሁም በቀጣዩ አምስት ዓመት ሶማሊላንድን በጥሩ አስተሳሰብና በልማት ጎዳና እንደምማራቸው በመግለፅ ረጅም ንግግር አድርጓል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ አዲሱ ፕሬዝዳንት  ከጎረቤት ሀገራትና ከአለም መንግስታት ጋር የትብብር ግኑኝነቶችን የመፍጥርና የማጠናከር ስራን እንደሚሰሩም በመድረኩ ላይ ገልፆዋል፡፡   

በሌላ በኩል ከተለያዩ የጎረቤትና የአለም ሀገራት የመጡ ልዕኳኖች በስነ-ስርዓቱ ላይ ለሶማሊላንድ ህዝብ ያስመዘገባቸዉን የልማት፣ የሰላምና የድሞክራሲ ስኬቶችን በማድነቅ ለአዲሱ ፕሬዝዳንት በሶማሊላንድ የተጀመረዉን የልማት ጉዞ ቀጣይነት እንዲኖረው ጥሪያቸዉን አስተላልፏል፡፡