በአዲሱ የሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት የስልጣን ርክክብ ስርሥርዓት ላይ የተሳተፉ የኢ.ሶ.ክ.መ.ልዑካን ቡዱኑ ወደ ክልሉ ርዕስመዲና ተመለሱ


ጅግጅጋ
(cakaaranews)ሀሙስ ታህሳስ 5/2010.በኢትዮጵያ ሶማሊ ክልል መንግስት /ፕሬዝዳንትና የከተማ ልማትና ኮንስተረክሽን ቢሮ ሃላፊ አቶ አብዲሀኪም ኢጋል ኡመር የሚመራ ልዑካን ቡዱን በቅርቡ የሶማሊላንድ የፕሬዝዳንትነት ምርጫ ያሸነፉት አቶ ሙሴ ቢሂ በሶማሊላንድ ርዕሰመዲና በሀርጌሳ ከተማ የተደረግላቸው የስልጣን ርክክብና የሹመት ቃለመሀላ ስርሥርዓት ላይ የተሳተፉ የኢትዮጵያ ሶማሊ ክልል መንግስት ልዑኳን ወደ ክልሉ ዋና ከተማ የሆነችው ጅግጅጋ ከተማ  ተመለሱ።

  በተጨማሪም በሶማሊላንድ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚንስተር አቶ ያሲን መሀሙድ ሂር የሚመራ የሶማሊላንድ ከፍተኛ ልዑካን ለኢትዮጵያ ሶማሊ ክልል ልዓኳንንእስከ ድንበሯ ቶግወጫሌ ከተማ ድረስ የሽኝት ፖሮግራም አደርጎላቿል።የሶማሊላንድ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚንስተሩ አቶ ያሲን መሀሙድ የኢትዮጵያ ሶማሊ ክልል ልዓኳን፤የኢትዮጵያ ሶማሊ ክልል መንግስትና ለሀገሪቱ ህዝቦችም በሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት የስልጣን ርክክብና ቃለመሀላ ስርሥርዓት ላይ ያሳዩት የወንድማማችነትና የመልካም ጉርብትና ባህልን የላቀ ምስገና አቀርቧል።


የኢ
.... ምክት ፕሬዝዳንት አቶ አብዲሀኪም ኢጋል ኡመር በበኩሉ ለሶማሊላንድ አመራርና ለህዝብ የሶማሊላንድ ድንበር ከደረሱበት ቀን ጀምሮ ላደረጉለት ደማቅና የአማሬ አቀባበልና ያሳዩት የእንግዳ ተቀባይነትን ባህላቸውም አመስግኗል። /ፕሬዝዳንቱ  ለሶማሊላንድ አዲሱ ፕሬዝዳንት መልካም የስራ ዘመን እንድሆንላቸው ከመመኘታቸው ባሻገር የኢትዮጵያ ሶማሊ ክልል መንግስትና ህዝብም ከሶማሊላንድ አዲሱ ፕሬዝዳንት መንግስት ጋር የላቀ ግንኘነት እንደሚፈጠሩም ገልጿል።

 

የኢትዮጵያ ሶማሊ ክልል ልዓካን ቡዱኑ ዛሬ ከሳዓት በኃላ በክልሉ ርዕስመዲና በጅግጅጋ ከተማ ገብቷል።