የኢ.ሶ.ክ.መ.ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አብዲ ሞሀሙድ በኦሮሚያ ክልል የተጨፈጨፉ የሶማሌ ተወላጅ ቤተሰቦች የሀዘን መግለጫ ልኳል።

ጅግጅጋ(cakaaranews)ሰኞ፤ታህሳስ 9 ቀን፤2010ዓም. የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አብዲ መሀሙድ ኡመር በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ሀረርጌ ዞን፤በዳሮለቡ ወረዳ ጋዱላ ቀበሌ በጭከኔና ዘግናኝ መልኩ የተጨፈጨፉ ንጹሃን የኢትዮጵያ ሶማሌ ተወላጅ ቤተሰቦች፤ ዘመድ አዝማድና ለመላው የሀገራችን ህዝቦች የተሰማቸው መራራና ጥልቅ ሀዘን በመግለፅ፤ለሟች ቤተሰቦችና ለሀገራችን ህዝቦች መጽናናት መኝቶላቿል።  .

በተጨማሪም በግፍና በኢ-ሰብኣዊ  የተጨፈጨፉ የሶማሌ ቤሔር ተወላጆች አምላክ ነብሳቸውን ገነት ያኖረው ብሏል ለሟች ቤተሰቦችና ዘመድ አዝማድም መጽናናትና መልካም ትግስ መኝቶላቿል ክቡር ፕሬዝዳንቱ።

በሌላ በኩል የክልሉ አገር ሽማግሌዎች በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ሀረርጌ ዞን፤በዳሮለቡ ወረዳ ጋዱላ ቀበሌ በጭከኔ የተጨፈጨፉ ንጹሃን የኢትዮጵያ ሶማሌ ተወላጅ ቤተሰቦች፤ ዘመድ አዝማድና ለመላው የሀገራችን ህዝቦች የተሰማቸውን መራራ በመግለጽ ለሟች ቤተሰቦችም መጽናናት መኝቶላቿል።