የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት በኦሮሚያ ክልል ውስጥ በጅምላ የተጨፈጨፉ የኢትዮጵያ ሶማሌ ተወላጆች የመንግስት አቋም መግለጫ ተሰጥቷል

ጅግጅጋ (Cakaaranews) እሮብ፤ ታህሳስ 11ቀን 2010ዓ.ም.በኦሮሚያ ክልል ምዕራ ሀረርጌ በዳሩለቡና በሐዊጉዲና ወረዳዎች ስር ከሚገኙ ቀበሌዎች ለደህንነታቸው ሲባል በአቅራቢያው በሚገኘው ፖሊስ ጣቢያዎች ተጠልሎ የነበሩትና በኦሮሚያ ክልል ለዘመናት ያህል የኖሩትየኢትዮጵያ ሶማሌ ተወላጅዜጎች በዘግናኝ መልኩ በጅምላ መጨፍጨፋቸው የሚታወስ ሲሆን በጉዳይ ዙሪያ ትክክለኛ መረጃ የሚያጣራ  ግብረኃይል  በፈዴራል መንግስት የተቋቋመ ቢሆንም፤ይህ ጸያፍ ድርጊት ከተሰማ ቀን ጀምሮ ለአንድ አፍታ ያህል ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይልከግድያ የተረፉት ዜጎች ህይወት ለመዳን ሲል ከፈዴራል መንግስት ጋር በኦሮሚያ ክልል ውስጥ በሶማሌ ቤሄረሰብ ላይ የተፈጸመው የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ያለውን መረጃ በይፋ እንድያወጡ ከፍተኛ ጥረት ሲያደርግ የነበረው የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት በጉዳዩ ዙሪያ  ያለው እውነታ መረጃ እንድሰጠን አደርገናል።

እነሆ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልላዊ መንግስት ም/ፕሬዝዳንትና የከተማ ልማትና ኮንስተራክሽን በሮ ኃላፊ ክቡር አቶ አብዲሀኪም ኢጋል ና የክልሉ መንግስት ኮሙኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢዲሪስ እስማኢል ይህ አሳዛኝ ክስተት በታህሳስ 6/2010ዓ.ም. እንደሰሙና ወዲያውም ከፈዴራል መንግስት በተላይ ከፈዴራል የጸጥታ አካላት ጋር መረጃ እንደተለዋወጠና በግምት ጭፍጨፋ የተከሰተበት አከባቢ ወደ 80 ኪ.ሚ. ርቀት ላይ የነበሩ የኢ.ፈ.ዴ.ሪ.መከላኪያ ሰራዊት አባላት በአስቹኳይ ከግድያ የተረፉት ዜጎች ህይወት ለመዳን ወደ አከባቢው ቢያመሩም በመኪና ለ2ሳዓት ያህል ልወስድባቸው የነበረው መንገድ በርካታ እንቅፋቶች እንደመንገድ መዝጋት፤በመንገዶች ላይ ጎማ ማቃጠል፤በመከላኪያ ላይ ጦርነት መክፈትና መሰል ችግሮች በሰራዊቱ ላይ መጋጠሙና በእግር እንድገሰገሱ ግድ እንደሆኖባቸው አረጋግጦናል።በተጨማሪም በእግር የተጓዙ መከላኪያ ሰራዊት በዳሩለቡ ወረዳ ሀሮሮቲ ቀበሌ በመስጅድ ተደብቆ የነበሩት 53 የሶማሌ ግለሰቦች አድኗል፤53 ሶዎቹ ከነሱ ጋር የነበሩ ግለሰቦች እንድተወሰደባቸውና ምን እንደተደረገባቸው መረጃ እንደለላቸው ለሰራዊቱ ገልጿል።ከዛም መከላኪያ ሰራዊቱ ያገኙት 53 ሶዎችን ይዞ ጉዞኣቸው እንደቀሉና ሌሊት 7ሳዓት የዘር ማጥፋት ጥቃቱ የተካሄደበት ጋዱላ ቀበሌ እንደገቡና በከተሟ ዳር ላይ በፓሊስ ጣቢያ ተጠልሎ ከነበሩትና በፖሊስ ጣቢያው ውስጥ በጅምላ ከተጨፈጨፉት 63 የኢት-ሶማሌ ቤሔር ተወላጆች አባል የነበረ አንድ ወጣት ልጅ ማገኘታቸውና ልጁ ልክ በጓደኞቹ ላይ ግድያ እንደተጀመረ ከፖሊስ ጣቢያ ግድግዳ ዘሎ በማምለጡ አምላክ እንዳተረፈ ነው የስራ ሃላፊዎቹ ያረጋገጠልን።

የክልሉ ም/ፕሬዝዳንት አቶ አብዲሀኪም ኢጋልና የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ አቶ ኢድሪስ ኢስማኢል የኢ.ፈ.ዴ.ሪ.መከላኪያ ሰራዊት ከአከባቢው ማህበረሰብ ጋር በመሆን ከቤት ንብረታቸው የተፈቀሉ የሶማሌ ቤሔር ተወላጆች ወደ ቄያቸው ለማስመለስና ተጨፍጭፎ በጅምላ የተቀበሩት አስኪሬኖችም ማውጣታቸውን ገልጿል።

በተመሳሳይም በታህሳስ 7 ቀን 2010ዓ.ም. በመከላኪያ ሚንስቴር አቶ ሲራጅ ፈጌሳ የሚመራ የፈዴራል ልኳን ቡዱን በጅምላ የተገደሉ ሬሳዎች ለማገኘትና የተገደሉ ሶዎች ቁጥር በተመለከተ  ትክክለኛ መረጃ ለማጣራት ያህል ሶዎች በተጨፈጨፈበት አከባቢ በሄሊኮብተር መጎበኘታቸውና በዛው እለት ከሳዓት በኋላ ወደ አዲስ አበባ ተመልሶ የፈዴራል መንግስት በጅምላ የተጨፈጨፉ ዜጎች የተቀበሩበት ጉድጓዶች ተቆፍሮ በጅምላ የተቀበሩ ሬሳዎች እንድያወጡና ጉዳዮ በትክክል እንድጣራ መወሰናቸው ገልጿል።በአከባቢው የተሰማሩ የፈዴራል መንግስት ልዑካን ቡዱን መካከል የኢ.ፈ.ዴ.ሪ.መከላኪያ ሚንስተር አቶ ሲራጅ ፈጌሳ፤ የፈዴራለና አርቢቶአደር ልማት ጉዳዮች ሚንስተር አቶ ከበዴ ጫኔ፤የፈዴራል ዋና አቃቢህግ አቶ ጌታቸው አምባዬ፤የኢትዮጵያ ሰብኣዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽኔር ዶር አዲሱ ገ/ኢግዛቤሔርና ከኦህዴድ ጽ/ቤት የመጣ አቶ ብርሃኑ እንደነበሩ የክልሉ ባላስልጣናት አረጋግጧል።

   

በተጨማሪም የኢ.ፈ.ዴ.ሪ.መንግስትፈዴራል የኢትዮ-ሶማሌ ቤሔር ተወላጆች በጅምላ የተቀበሩት ጉድጋዶች ውስጥ ያሉት አስኪሬኖች ለማውጣት የተቋቋመ ዶርተሮች፤ኔርሲንግዎችና የሀገር ውስጥ ሚዲያ አካላት ያቀፈ ግብረሃይል በሁለት ሄሌኮብተሮች መሰማራታቸውና በጅምላ የተቀበሩት በርካታ ቁጥር ያላቸው ሬሳዎች ማውጣታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ ገልጿል።

የክልሉ ም/ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አብዲሀኪም ኢጋልና የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ ኢንጅኔር እድሪስ እስማኢል እንደገለጹልን የፈዴራል ግብረኃይሉና የመከላኪያ ሰራዊት አባላቱ እስካሁን በቆሻሻ ጉድጓዶች በጅምላ የተቀበሩ 48 አስኪሬኖችና 4 ከባድ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ግለሰቦች እንዳገኙና 10 የጅምላ መቃብር ጉድጓዶችም እየተቆፈረ ይገኛል።በተመሳሳይም በዳሩለቡ ወረዳ በሁሉቆ ቀበሌ 4 ሰው እንደተገደሉ፤በተምሳ ቀበሌ 24 ንጹሃን ዜጎች መግደሉና በቆረቲ ቀበሌም 18 ንጹሃን ዜጎች በኦሮሚያ ጸጥታ አካላት ተጨፍጨፎባቿል።

በሌላ በኩል የኢ.ፈ.ዴ.ሪ.መከላኪያ ሰራዊቱ በተለያዩ የምዕራብ ሐረርጌ ዞን አከባቢዎች ይኖሩ የነበሩ የሶማሌ ማህበረሰብ ከመግደል ማደናቸው ኃላፊዎቹ ገልጿል በነዚህ አከባቢዎች መካከል በሶሮሮ ቀበሌ 100 ሶዎች አድኗል፤በመቻሬ 300 ሶዎች ከመግደል ያተረፉ ሲሆን በወታደራ ቀበሌም 301 የሚሆኑ የኢትዮጵያ-ሶማሌ ቤሔር ተወላጆች በጀግናው መከላኪያ ሰራዊት እገዛ እንደተረፉ አረጋግጦልናል።

በሌላ በኩል ይህ ከአሁን በፊት ድርጊት በሶማሌ ክልል መንግስት ላይ ሲወቀስ የነበሩት ምንጭ አልባና አወዛጋቢ ሀተታዎች ከእወነት የራቀ ውሸትና የበሬወለድ ፖሮፖጋንዳ መሆናቸው ለፈዴራል መንግስትና ለሀገሪቷ ህዝቦችም በግልጽ ያሳያልብሏል።በተጨማሪም የዘር ማጥፋት ድርጊቱ የተፈጸመበት አከባቢው መሀል ኦሮሚያ በመሆኑና ከሶማሌ ክልል ጋር በሁሉም አቅጣጫ ምንም አይነት የወሰን ግንኙነት የለሌ አከባቢ ሆኖ አንዳንድ የኦሮሚያ ክልል ባላስልጣናቱ ለVOAአማራኛ የሰጡት መረጃ የሶማሌ ልዩሃይል ነው የወረሩን በማለታቸው እጅግ የሚገርሚና በጣም የሚያሳዝን ስብኢና የለለ ሃሳብ መሆኑን የሶማሌ ክልል ባላስልናቱ አትቷል።የዚህ የዘር ማጥፋት ጨፍጨፋ ድብቅ አጀንዳና አለማው የሀገሪቱ ህግመንግስት፤የፈዴራሊዝም ስርዓትና የህዝቦች ሰላምና እንድሁም የህዝቦች አብሮ የመኖር እሴቶችን ለማደፍረስ የተደረገ ጥረት ሲሆን የሀገሪቱ ንጹሃን ህዝብ ጭካኔ በተሞላ መልኩ እንደባዳ በጅምላ ጨፍጨፎ አሁንም በአደባባይ መካዱና ለሚዲያ የውሸት ርፖርት መስጠታቸው አቢይ ማስረጃ ነው ብሏል።

በተጨማሪም የክልሉ መንግስት ለመላው የሀገራችንና ለክልሉ ህዝቦች እንድሁም ለሟች ቤተሰቦችና ዘመድ አዝማድ የተሰማቸው መራራ ሀዘን በመግለጽ፤ ለፈዴራል መንግስትና ለቤሔራዊ ጸጥታ ተቋማት በኦሮሚያ ክልል ውስጥ የሚኖሩ የሶማሌ ቤሔር ተወላጆች ህይወት ለማዳን ላደረጉት ጥረት የክልሉ ባላስለጣናት የላቀ ምስገና አቀርቧል።ለሟች ቤተሰቦችም የክልሉ መንግስት አስፈላጊው ድጋፍ ሁሉ እንደሚደረግላቸው ከመናገራቸው ባሻገር ፤ይህንን ድርጊት የፈጸሙት ጥቅት ግለሰቦች የኦሮሞ ህዝብ የማይወከሉ ናቸው ብሏል።በተማሪም የሶማሌና ኦሮሞ ህዝቦች ለዘመናት አብሮ የኖሩና በእምነት፤በባህልና በደም የተሳሰሩና የማይነጣጠሉ ወንድማሞች ህዝቦች መሆናቸውን ሃላፊዎቹ አብራርቷል።በመጨረሻም የክልሉ መንግስት በሁለቱ ወንድማሞች ህዝቦች ሰላምና ማረጋጋት ቀን ተሌሊት እነደሚሰራም ባላስልጣናቱ አስገንዝቧል።