የወቻሌ ከተማ አስተዳደር ለ400 ወጣቶች የሥራ እድል ፈጠራ ገንዘብ አስረክባቿል

ከወቻሌ ከተማ አስተዳደር(Cakaaranews) አርቢ፤ታህሳስ 13ቀን/2010ዓ.ም.የወቻሌ ከተማ አስተዳደር ከአሁን በፊት የከተሟ ወጣቶች በስራ እድል ፈጠራ ፖሮግራምን ተጠቃሚ ለማድረግ በ22 የህብረት ስራ ማህበራት የተደራጁ 400 ወጣቶችን የ6 ሚልዮን ብር አስረክቧል።

በመድረኩ ላይ የክልሉ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሃላፊና የፕሬዝዳንት የሚዲያ ዘርፈ አማካሪ አቶ መሀመድ ቢሌ ሀሰን እና የቶግወቻሌ ከተማ አስተዳደር ካንቲባ አቶ መሀሙድ አብዲ ሙሁመድ እንዱሀም የከተማ አስተዳደሩ ወጣቶች ተሳትፏል። በተጨማሪም በወጣቶች ሥራ እድል ፈጠራ መድረኩ ላይ ተገኝቶ ንግግር ያደረጉት የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሃላፊና የፕሬዝዳንት የሚዲያ አማካሪ አቶ መሀመድ ቢሌ ሀሰን  የወጣቶች ሥራ እድል ፈጠራ ፖሮግራሙ በአገር አቃፍ ደረጃ ወጣቶችን ከስራ አጠነት ለማላቀቅ የታቀደ መርሃግብር መሆኑን ከመግለጻቸው ባሻገር ወጣቶቹ ይህ ከነሱ በፊት የነበሩት ወጣቶች ያላገኙት ውድ እድልን ተጠቃሚነታቸው እንድያሳዱና በይቻላል መንፈስ ራሳቸው እንድቻሉ አሳስቧል።የወጣቶች ስራ እድል ፖሮግራሙ የሀገራችን ወጣቶች ዋነኛ ጠላት የሆነውን ደህነት ለማጥፋት፤ ያለው ብቸኛ አማራጭ ነው ብሏል ቢሮ ሃላፊው።

የወጫሌ ከተማ አስተዳደር ካንቲባ አቶ መሀሙድ አብዲ በበኩሉ በ22 የወጣቶች ስራ ፈጣራ ህብረት ስራ ማህበራት የተደራጁ 400 ወጣቶቹ ለስራ ፈጠራ የተመቻችላቸውን ገንዘብ ለታለሚለት አላማ እንዳሳኩና በከተሟ አንድም ወጣት በስራ አጠነትና በአመለካከት ችግር መቀመጥ እንደለሌባቸው አስገንዝቧል።

በመጨረሻም በህብረትና ማህበራት የተደራጁ ወጣቶች በበኩላቸው የክልሉ መንግስት ለወጣቶች ስራ ፈጠራ ያመቻችለት ገንዘብ ተጠቃሚ በማድረጋቸው እጅግ ደስተኛ ከመሆናቸው ባለፈ የተሰጣቸው ገንዘብ በታቀድለት አግባብ እንደሚጠቀሙበትና  ሀገራችን ደህነትን ለማፍጣት የሚታደርገው የህዳሴ ጉዞ የበኩላቸው ኃላፊነት እንወጣለን ብሏል።