የኢ.ሶ.ክ.መ.ካፍተኛ ልዑኳን ቡዱንና በሰሜን አሜሪካ የሚኖሩ ዲያስፖራ አካላት ጋር በሚኒያፖሊስ ከተማ የጋራ ምክክር መድረክ አደረጉ

ሚኒያፖሊስ(cakaaranews)ሰኞ፤ታህሳስ 16/2010. የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት ካፍተኛ ልዑኳን ቡዱን በሰሜን አሜሪካ የሚኖሩ የክልሉ ተላጅ ዲያስፖራ አባላት የጋራ ምክክር መድረክ በሚኒያፖሊስ ከተማ አካሄዷል።

በኢ.ሶ.ክ.መ.የእንስሳትና አርቢቶአደር ልማት ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ መጂዳ መሀመድ የሚመራ የክልሉ መንግስት ካፍተኛ ልዑኳን ቡዱን በሰሜን አሜሪካ በሚነያፖሊስ ከተማ ከክልሉ ተላጅ ዲያስፖራ አባላት ጋር በክልሉ እየተከናወነ ባሉ የልማት፤የመልካም አስተዳደር፤ዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታና በክልሉ ያለው ዘርፈ-ብዙ የኢንቬስትመንት እድሎችና እንድሁም በክልሉ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተመካክሯል።በመድረኩ ላይም የክልሉ ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አብዲ መሀሙድ ኡመር በቪድዮና በስልኪ ኮንቨሬንስ ተሳትፏል።በተጨማሪ በልዕካን ቡዱኑ መካከልም የክልሉ ንግድ፤ትራንስፖርቲና እንዱስተሪ ቢሮ ሃላፊና የኢ.ሶ.ህ.ዴ.ፓ.የድርጅት ጉዳዮች ሃላፊ አቶ ከድር አብዲ እስማኢል ፤የክልሉ መስተዳደር ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አብዲመሀድ መሀመድ አባሴ ይገኙበታል። በመጀመሪያም የክልሉ ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አብዲ መሀሙድ አብዲ መሁድ ኡመር በክልሉ የተሰሩ ሰፊ የልማት፤የሰላምና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች በስልኪ አቀርቧል።

በኦሮሚያ ክልል ውስጥ በምዕራም ሀረርጌ ይኖር የነበሩ የኢትዮጵያ ሶማሌ ተወላጅ ቤተሰቦች፤ዘመድ አዝማድና ለመላው በተላይ የክልሉና የሀገሪቱ ህዝቦችባሉበት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን መልዕክታቸው በማስተላለፍ የሁለቱ ክልሎች ግጭትን ለማስቆም የሁለቱ ክልል መንግስታት የሁለቱ ህዝቦች መካከል ዘላቂ ሰላም ለማምጣት በከፍተኛ ጥረት እየሰሩ መሆኑን አብራርቷል።የክልሉ መንግስት በመጨረሻ አመታት ያከናወናቸው ዘርፈብዙ የዘላቂ ልማት ፖሮጀክቶችና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ማከናወናቸውን የክልሉ ተወላጅ ዲያስፖራ አባላት ከፍተኛ እንደነበረና አሁንም አገሪቱ ከደህነት ለማላቀቅና ሀገራችን መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገራት ተርታ ለማሳለፍ የሚናደርገው ጥረት የዲያስፖራ ትስስር ከፍተኛ መሆኑን ፕሬዝዳንቱ ጠቆሟል።

በሌላ በኩል በመድረኩ ላይ የተገኙት የክልሉ የእንስሳትና አርቢቶአደር ልማት ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ማጂደ መሀመድ መሀሙድና የክልሉ ንግድ፤ትራንስፖርቲና እንዱስተሪ ቢሮ ሃላፊና የኢ.ሶ.ህ.ዴ.ፓ.የድርጅት ጉዳዮች ሃላፊ አቶ ከድር አብዲ እስማኢል ፤የክልሉ መስተዳደር ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አብዲመሀድ መሀመድ አባሴ ምክክር መድረኩ በክልሉ መንግስትና ህዝብ የተከናወኑ የልማትና መልካም አስተዳደር ተግባራት መተራመስ የሚፈለጉና በክልሉ ማህበረሰብ ስም የሚነገዱት ጥቅት ጽንፈኛ የዲያስፖራ አባላት ለመቃወም ትልቅ ሚና እንደሚጫወት አስገንዝቧል።በተጨማሪም የክልሉ ህዝብ ባለፉት ስርዓቶች ላይ የሳለፉት መራራ የልማት እጦትና ህዝቡ የቻለው ሰቀቀን ታሪክንም ባላስልጣናቱ አስረድቷል።በተመሳሳይም የክልሉ መሪ ድርጅት ኢ.ህ.ዴ.ፓና የክልሉ መንግስት በተላይ በመጨረሻ አመታት ላይ የክልሉ ህዝብ ኑሮ ለማሻሻል በንጹህ የመጠጥ ውሃ፤በጤና፤በትምህርት፤በግብርና በመንገድና ድልድሎች ፤በመብራት፤በወጣቶች ስራ እድል ፈጠራና በከተማ ልማት እንድሁም ክልሉ በሁሉም መስረተ ልማትና በሁሉም የኢኮኖሚክ ልማት ጉዳዮች ዙሪያ አመርቂ ስራዎች መስራታቸውን አመራሩ ጠቆሟል።በሰሜን አሜሪካ በተላይም በሚኒያፖሊስ የሚኖሩ የክልሉ ተላጅ ዲያስፖራዎች ይህንን መድረክ ባማሬ መልኩ በማዘጋጀታቸውና በደማቅ ሁኔታ መሳተፋቸውን የላቀ ምስገና አቀርቧል።

በተመሳሳይም በመድረኩ መፍቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የክልሉ የክልሉ ዲያስፖራ አካላት ክልሉ የመንግስት በልማት፤በጸጥታ፤በመልካም አስተዳደርና በህዝብ ግንኙነት፤ እንድሁም በዲያስፖራ ትስስርና ትብብር ለማጠናከር እያደረገ ያለው ስራዎች ደስተኛ ከመሆናቸው ባሻገር በክልሉም ሆነ በሀገሪቱ ሰላምና ልማትን እንቅፋት የሚሆኑበት ማንኛውም ጠላት እንደሚታገሉ ገልጿል።