የኢትዮጵያ ሶማሌ ህዝብ ዴሞክራሲ ፓርቲ ማዕካላዊ ኮሚቴ መደበኛ ጉባኤ በድል ተጠናቀቀ

ጅግጅጋ(Cakaaranews)ሀሙስ፤ታህሳስ 19/2010ዓ.ም. ከታህሳስ15 እሰከ ታህሳስ 18ቀን፤2010ዓ.ም በተለያዩ ርዕስ-ጉዳዮች ሲገመገም የነበረውን የኢ. ሶ.ህ.ዴ. ፓ. ማዕካላዊ ኮሚቴ  መደበኛ ጉባኤ ዛሬ ካሳዓት በኋላ በድል ተጠናቀቀ ።

ጉባኤው የመሩት የኢ. ሶ.ህ.ዴ. ፓ. ሊቃመንበርና የክልሉ ም/ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ መሀመድ ኢሳቅና የኢ. ሶ.ህ.ዴ. ፓ. ም/ሊቃመንበርና  የክልሉ ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አብዲ መሀሙድ ኡርመር  ሲሆን በጉኤው ላይ ከነበሩት አጀንዳዎች መካካል በ2010ዓ.ም እቅድ አፈጻጸም በተላይ በውሃ፤በእንስሳት መኖ፤በግብርና፤በትምህርትና በጤና መስኪ ትኮር እቅድ አፈጻጸም፤በውሃ ዝርጋታና በጥልቅ የውሃ ጉድጓዶች የተሰሩ ሥራዎች፤የክልሉ ዞኖች፤ወረዳዎችና ቀበሌዎችን የሚያስተሳሰሩ መንገዶችና ድልድሎች የተከናወኑ ስራዎች፤በመልካም አስተዳደርና ፍትህ ስራዎችና በጸጥታ ዘርፍ በተላይም በምዕራብ ሀረርጌ የተጨፈጨፉ ዜጎች ሪፖርትና ለኢትዮጵያ ሶማሌ ተፈናቃይ ወገኖች የተደረገላቸው ድጋፍና ለወደ ፊትም ለሚደረግላቸው ድጋፍና የመልሶ ማቋቋም፤እንድሁም በሀገር ውስጥና በውጭ አገርም የተሰሩ የድርጅትና የህዝብ ግንኙነት ስራዎችም በጥልቀት ተገምግሟል።

በድርጅቱ ማዕከላዊ ኮሚቴ ጉባኤ መክፈቻ ላይ የክልሉ ም/ፕሬዝዳንትና የከተማ ልማትና ኮንስተራክሽን ቢሮ ሃላፊ ክቡር አቶ አብዲሀኪም ኢጋል ኡመር በቅርቡ በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ሐረርጌ የተጨፈጨፉት የሶማሌ ቤሔር ተላጅ ወገኖች ላይ እንደ ክልል መንግስትና እንደ ድርጅትም የተሰሩ ስራዎች ሪፖርት አቀርቧል።በተጨማሪም ም/ፕሬዝዳንቱ የሶማሌ ተፈናቃይ ወገኖች መልሶ ማቋቋም ኮሚቴ ሊቃመንበር ስለነበሩ በፈዴራል መንግስቱ በምዕራብ ሐረርጌ የተጨፈጨፉት የሶማሌ ቤሔር ተላጅ ወገኖች ላይ ላደረጉት አስታዋጾም በሪፖርቱ ያካተቱ ሲሆን ለተፈናቃይ ወገኖች የተደረግላቸው ድጋፍና ለቀጣይም የሚደረግላቸው የመልሶ ማቋቋም እቅድም ለኮሚቴው አቀርቧል።

በሌላ በኩል የክልሉ ም/ፕሬዝዳንትና እንድሁም የግብናና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ሱኣድ አህመድ ፋራህ  የህዝብ ኑሮ ለማሻሻል የታቀደውና በውሃ፤በእንስሳት መኖ፤በግብርና፤በትምህርትና በጤና መስኮች ትኮር እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት አቀርቧል።

በተመሳሳይም የኢ.ሶ.ህ.ዴ.ፓ.ማዕካላዊ ጽ/ቤት የፖለቲካ ጉዳዮች ሃላፊ አቶ ኡመር መሀሙድ  በሀገር ውስጥና በውጭ አገርም የተሰሩ የድርጅትና ህዝብ ግኙነት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ለኮሚቴው አቀርቧል።

ከበርካታ ውይይቶችና ግምግማዎች በኋላ የድርጅቱ ማዕካላዊ ኮሚቴ አባላቱ በልማትና በጸጥታ ዘርፍ በተላይም በንጹህ መጠጥ ዉሃ፤በመንገዶችና ትላልቅ ድልድዮች፤በግብርና፤በትምህርት፤በጤና፤በወጣቶች ስራ እድል፤በድርጅት ጉዳዮችና እንድሁም በህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽንና በመልካም አስተዳደርም የተሰሩ ሥራዎች አመርቂ በመሆናቸው ከስር አስምሮበታል።በተጨማሪም የድርጅቱ ማዕካላዊ ኮሚቴ አባላቱ የ2010ዓ.ም. የመንግስትና የፓርት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።

በሌላ በኩል በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ለዘመናት የኖሩት በንጹሃን የሶማሌ ቤሔር ተወላጆች ላይ የተፈፀመውንና በአገራችን ታሪክ ተሰምቶና ታይቶ የማይታወቀው አጸያፊ የጅምላ ጨፍጨፋ ድርጊትን አውግዟል።በተጨማሪም የሟች ቤተሰቦችና ዘመድ አዝማድም የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን መልዕክታቸውን አስተላለፏል።

 በመጨረሻም ማዕካላዊ ኮሚቴው የ2010ዓ.ም.እቅድ አፈጻጸም በመገምገም ለተገልጋዩ ህዝብ ስራዎች ማጠናከር እንዳለበት፤ የሰላምና ጸጥታ በተላይም በኢትዮጵያሶማሌና ኦሮሚያ ክልል ወሰን አከባቢ ግጭቶችን ማስቆምና ዘላቂ ሰላምን ለማምጣት ሰፊ ስራዎች መስራት እንዳለባቸው እንደቀጣይ ልማት አቅጣጫዎች አስቀጧል።በተጨማሪው ድርጅቱ ከምን ግዜም በላይ የሁለቱ ወንድማሞች ለማቀራረብና ለማስታረቅ እንደሚሰራ ገልጿል።