ፕሬዝዳንት አብዲ መሀሙድ ኡመር ወደ አገሪቱ ርዕስመዲና አመሩ

አዲስ አበባ(Cakaaranews)መክሰኞ፤ታህሳስ 24ቀን 2010ዓ.ም.በኢ.ሶ.ክ.መ. ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አብዲ መሀሙድ ኡመር የሚመራና 25 የክልሉ ካቢኔ አባላት ያቀፈ ከፍተኛ ልዑካን ቡዱን ከክልሉ ዋና ከተማ ወደ የሀገሪቷ ርዕስመዲና የሆነችው አዲስ አበባን አቀኑ። ልዑካን ቡዱኑ ከአዲስ አበባ ወደ መቀሌ ከተማ እንደሚያልፉም ተውቋል።በሌላ በኩል ለሚቀጥለው ቀናት በትግራይ ክልል ርዕስ ከተማ በመቀሌ ለሚካሄደው የ5ቱ ኢህአዴግ አጋር ድርጅቶች ማላትም የኢ.ሶ.ህ.ዴ.ፓ.፤የአ.ብ.ዴ.ፓ.፤ሐ.ብ.ሊ.የጋህዴንና የቤ.ጉ.ሕ.ዴ..አ.ግ. ድርጅቶች ባለፈው 18 ቀናት የፈጀው የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ጥልቅ ተሀድሶ ግምገማ ህደት፤በግምገማው ላይ የነበረው ሂስና ግለ ሂስ፤በግምገመው የተወሰዱት እርምጃዎችና እንድሁም ከኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ግምገማ የወጡት የትክረት አቅጣጫዎችን ወደ ታች ለማውረድ የሚመክርበት ጉባኤ ይሳተፋሉ።