የኢትዮጵያ ሶማሌ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርት በራሶ ከተማ ከህዝቡ ጋር ሰፊ የጋራ መግባባት መድረክ የአካሄዳል

ጅግጅጋ(cakaaranews)hሀመሙስ ታህሳስ 26/2010ዓ.ም.በቀጣዩ ሳሚንት በአፍዴር ዞን በራሶ ወረዳ መቀመጪያ በራሶ ከተማ የክልሉ መሪ ድርጅት ኢ.ሶ.ህ.ዴፓ. ከክልሉ ህዝብ ጋር ክልሉ ባለፈው 7አመታት ባሳለፈው የልማት፤የመልካም አስተዳደርና የዴሞክራሲ እንድሁም የታዩ ተግዳሮትና በቀጣይ የልማት፤የጸጥታና የመልካም አስተዳዳር ትክረት አቅጣጫዎችን የሚወያይበት ሰፊ መድረክ ያካሄዳል።

በሌላ በኩል እንደሚታወቀው ከቅርብ አመታት በፊት ራሶ መንደር እንደነበረች ይታወቃል ይህ ደግሞ በክልሉ መንግስት ቁርጠኝነት የትላንትናው ራሶ ቀበሌ ወረዳ በማድረጉና ከተሟ ከእለት እለት እደገች በመምጣቷ ዛሬ በሺዎች የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ ሶማሌ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርትና ህዝብ በሚወያይበት መድረክ ለሚካፈሉ ታሳታፊዎች ለሚያስፈልገው ጉዳዮች ሁሉ አሟልታ እንድታስተናግድ ምክንያት ሆኗል።