ነጻ የአይን ህኪምና አገልግሎት በጅግጅጋ ከተማ ተጀመረ

ጅግጅጋ(Cakaaranews) አርቢ ታህሳስ 27/2010.በጅግጅጋ ከተማ አስተዳደርና በአከባቢው የሚገኙና የተለያዩ የአይን በሽታ ችግር ያለባቸው ዜጎች ነጻ የአይን ህኪምና አገልግሎት የሚያገኙበት ፖሮግራም በዛሬ እለት በጅግጅጋ ዩኒቬርሲቲ የመለስ ዜናዊ መታሰቢያ ሪፊራል ሆስፒታል ተጀመረ

የጅግጅጋ ዩኒቬርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶር አብዱልአዚዝ ኢብራህም  ይህ ነፃ የአይን ህኪምና አገልግሎት ለአንድ ሳሚንት ያህል የሚሰጥ ፖሮግራም ሲሆን በጅግጅጋ ከተማ አስተዳደርና በአከባቧ ለሚኖሩና በሺዎች የሚቆጠሩ የተለያዩ የማየትና የአይን ብርሃን በሽታ ያለባቸው ዜጎች ነጻ የአይን ህኪምና አገልግሎት ተጠቃሚ የሚሆኑበት ፖሮግራም ነው ብሏል።በተጨማሪም የጅግጅጋ ዩኒቬርሲቲ መለስ ዜናዊ መታሰቢያ ሪፊራል ሆስፒታል ከአሁን በፊት ይህንን የአይን ቀዶ ጥገና ህኪምና አገልግሎች የሚሰጥ ዲፓርትመንት ስላልነበረ ከወዲሁ ይህንን የአይን ቀዶ ጥገና ህኪምና አገልግሎት በቋሚነት እንደሚሰጥ ዲፓርትመንት ማቋቋምም ዶር አብዱልአዚዝ ገልጿል።

በመጨረሻም ከጅግጅጋ ከተማ አስተዳደርና ከጅግጅጋ አከባቢ መጥቶ ይህንን ነጻ የአይን ቀዶ ጥገና ሕክምና ተደርጎለት የአይነ-ብርሃናቸው የተመለሰላቸው ዜጎች በበኩላቸው ባገኙት የአይን ህኪም አገልግሎቱን እጅግ ደስተኛ መሆናቸውን ገልጿል።በተጨማሪም የክልሉ መንግስት ይህንን ነጻ የአይን ቀዶ ጥገና ሕክምና አገልግሎትን ለማብቃትና የአይነ-ብርሃናችን ለማስመለስ ባደረገው ጥረት አበረታች ነው ብሏል።