አስደንጋጭ ዜና፤ በምዕራብ ሐረርጌ ዞን በሚገኙ የኢትዮ-ሶማሌ ንጹሃን ዜጎች ላይ በተደረገው የምግብ ማቀቡ ለዜጎች ሞትና እልቅት አዳረገ

ከምዕራብ ሐረርጌ(cakaaranews)ሰኞ፤ታህሳስ 30 ቀን/2010..አሁንየደረሰንመረጃ እንደሚያረጋገጠው፤በኦሮሚያክልልምዕራብሐረርጌዞን በዳሩለቡና በሀዊ ጉዲና ወረዳዎች የሚኖሩ የኢትዮጵያ ሶማሌ ተወላጅ ንጹሃን ዜጎች በኦሮሚያ ክልል ውስጥ የሚገኙና እራሳቸው ቄሮ ብሎ የሚጠሩ አሸባሪ ቡዱን በሶማሌ ንጹሃን ተወላጆች ከነ እንስሳት ሀብታቸው ለበርካታ ቀናት በተወሰኑ አከባቢዎች አሰባስቦ፤ በንጹሃን ዜጎችሁ ላይ የጣሉበት የምግብ፤የዉሃ፤የመድሃኒትና ለሰው ልጅ አስፈላጊ ነገሮች ሁሉ ባደረጉት እገዳና ማቀቡ ባስከተለው ችግር ውስጥ ለረጅም ቀናት በመቆየታቸው ከትላንትና ጀምሮ እድሜያቸው ከ10 አመት በታች ለሆኑት 20 የኢትዮጵያ ሶማሌ ተወላጅ ህጻናት በተደረገባቸው በኢ-ሰብኣዊ ድርጊት በመሞታቸውና አሁንም አሸባሪ ቄሮ ቡዱኑ በንጹሃን ዜጎቹ ላይ እየፈጸሙባቸው ባለው የምግብ፤የመድሃኒትና አስፈላጊ እርዳታን ማቀብ በመጣሉ ምክንያት በዜጎችሁ ላይ ለከፋ ርሃብና ሞት እያጋለጠ መሆኑን የአከባቢው ምንጮች አረጋግጧል።

በሌላ በኩል አሸባሪው ቄሮ ቡዱን እስካሁን 4 ንጹሃን የሶማሌ ተወላጅ ዜጎች በሀዊጉዲና ወረዳ በሆየዴ ቀበሌ መግደላቸው ተሰምቷል።ይህ ችግር ደግሞ በቅርቡ የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ለ17ቀናት ያህል የካሄዱት ጥልቅ ግምገማ ላይ በሰለም፤በህግ የበላይነትና በህዝቦች አብሮ የመኖር እሴቶች ለማረጋገጥ  ሲባል መሪ ድርጅቱና የኢህአዴግ አባል የሆኑት ቤሔራዊ ድርጅቶቹ በጋራና በተናጠል ባወጡት መመሪያ ነጥቦች፤በኢ.ፈ.ዴ.ሪ. ቤሔራዊ የጸጥታ ም/ቤቱና በፈዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የወጣ መመሪያዎችሁ እንዳይሳካ ጸረ-ሰላሙ ቄሮ  የሚያደርጉት መሰናከልና እንቅፋት መሆኑን በግልጽ ያሳያል።