የህወሓት 7ተኛ ድርጅታዊ ኮንፈረንስ በመቐለ ከተማ ተጀመረ

መቐለ(Cakaaranews)አርቢ፤ጥር 3ቀን/2010.የህወሓት7ተኛድርጅታዊኮንፈረንስ  በትግራይ ክልል ርዕስመዲና በመቐለ ከተማ  በሚገኘውየሰማእታትሐውልትየመሰብሰቢያአደራሽተጀምሯል።በኮንፈረንሱ  ከ2500 በላይ የሚሆኑ የ4ቱ ኢህአዴግእህት ድርጅቶችና5ቱ አጋርድርጅቶችተወካዮችተገኝቷል፡፡

በዚህኮንፈረንስለመሳተፍ ከሶማሌ ክልል በኢ.ሶ.ህ.ዴ.ፓ. ም/ሊቃመንበርና የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት በክቡር አቶ መሀሙድ ኡመር የሚመራ 25 የኢ.ሶ.ህ.ዴ.ፓ.ከፍተኛ አመራር አባላት የያዘ ልዑካን ቡዱን ይገኛሉ።ከልዑካን ቡዱኑ መካከል የኢ.ሶ.ህ.ዴ.ፓ. ም/ሊቃመንበርና የኢ.ሶ.ክ.መ.ፕሬዝዳንት አቶ መሀሙድ ኡመር፤ የኢ.ሶ.ህ.ዴ.ፓ.ሊቀመንበርና የክልሉ ም/ቤት አፈጉባኤ አቶመሀመድረሺድ ኢሳቅና የክልሉ ም/ፕሬዝዳንትና የከተማ ልማትና ኮንስተራክሽን ቢሮ ሃላፊ አቶ አብዲሀኪም ኢጋል ኡመርተጠቃሽናቸው። በተጨማሪም ይህ የህወሓትድርጅታዊኮንፈረንስ በቀጣዩ ሳምንት ኢ.ሶ.ህ.ዴ.ፓ.በአፍዴር ዞን ፤በራሶ ከተማ በሚያካሄደው ድርጅታዊኮንፈረንስ ወሳኝ ግብዓት ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል  

በመጨረሻም በጉባኤው ከኢህአዴግ ስራ አሰፈጻሚ ኮሚቴ ጥልቅ ግምገማ የወጡት የልማት፤የሰላምና የመልካም አስተዳደር ትክረት አቅጣጫዎች ወደ ታች ለማውረድና ተግባራዊ የሚደረግበት የለውጥ አቅጣጫዎች ይወጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።