በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች አስመልክቶ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ምክርቤት አባላት ለሁለት ቀናት የሚቆይ ምክክር መድረክ እያካሄዱ ነው

ጅግጅጋ(Cakaaranews) አርብ ፤የካቲት 2/2010ዓ.ም.በወቅታዊሀገራዊጉዳዮችአስመልክቶየኢትዮጵያሶማሌክልልምክርቤት አባላት ለሁለት  ቀናትየሚቆይምክክርመድረክእያካሄዱ ነው።የምክርቤቱ አባላት ቀድሞ ከነበራቸው አመለካከት የተሻለ ግንዛቤ በማስጨበጥ ለአንድ አላማ እንድሰለፉ መድረኩ ይረዳል ብሏል የኢ.ሶ.ክ.መ. ምክርቤት አፈጉባኤ አቶ መሀመድረሺድ ኢሳቅ።

መድረኩ በዋናነት በክልሉ አጎረባች አከባቢዎች ቀደም ብሎ ለተፈጠሩ ችግሮች በሌሎች ላይ ጣት ከመቀሰር በዘለለ ከእኛ ጋር የነበሩ ክፍተቶች ምንድናቸው በሚል የሚናይበት ይሆናል ሲሉ የምክርቤቱ አፈጉባኤ ተናግሯል።  በተጨማሪም በአንድ ክልል የሚፈጠር ችግር በሌሎችም ላይ የማይቀር ሲሆን ኢትዮጵያን እንደሀገር ለማስቀጠል በሁሉም አቅጣጫ ያሉት ነባራዊ ሁኔታዎች መርዳት ያስፈልጋል ነው ያሉት የምክርቤቱ አፈጉባኤ አቶ መሀመድረሺድ ኢሳቅ።የተለያዩ ፈላጎቶችን መነሻ አደርጎ የተፈጠሩ ችግርች የህዝብ ለህዝብ ትስስርን እንዳይጎዱ ለማድረግ አመራሩ ልሄድባቸው የሚያስችሉ የትኩረት አቅጣጫዎች ማስያዝም ከምክክሩ የሚጠበቅ አንኳር አጀንዳ ነው ብሏል አፈጉባኤው።

በቅርቡ በአንዳንድ የሀገሪቱ ክፍሎች ለተፈጠሩ ሁከቶችና ችግሮችም ለማቅረፍ ከሌሎች ሀገራዊ ድርጅቶች ጋር አብረን በሚንሰራበት ወቅት ቀድሞ የታዩ ችግሮች እንዳይደገሙ ውጤታማ በሆነ መልኩ እንዴት በጋራ እንረባርባለን የሚለውም በውይይቱ ትኩረት እንደምሰጥበትም አቶ መሀመድረሺድ እሳቅ አክሎ ገልጿል።

በመጨረሻም ከም/ቤቱ ምክክር መድረክ በኢትዮጵያሶማሌና በኦሮሚያ  ክልሎች መሀከል የነበሩት ግጭቶችን አስወግደን፤እንደ ወንድማሞች፤እንደጎሮቤትና እንደ አንድ ሀገር ህዝቦች ሆነን ከኦሮሚያ አቻ ወንድሞቻችን ጋር እጅ ለእጅ ተያይዘን በሀገራችን ልማትና እድገት ጉዳዮቻችን ላይ አብረን የሚንዘልቅበት ውሳኔዎች እንደሚወጡም አፈጉባኤ መሀመድረሺድ እሳቅ አብራርቷል።