7ተኛው የኢ.ፈ.ዴ.ሪ. መከላኪያ ሰራዊት በዓል ቀን በጅግጅገጋ ተከማ በደማቅ ሁኔታ ተከብረዋል

ጅግጅጋ(cakaaranews)ሰኞ፤የካቲት 5/2010ዓ.ም. 7ተኛው የኢ.ፈ.ዴ.ሪ.ቤሔራዊ መከላኪያ ሰራዊት በዓል ቀን፤በኢትዮጵያ ሶማሊ ክልል መንግስት ርዕሰመዲና  በጅግጅገጋ ተከማ በአገራቀፍ ደረጃ በአማረ ሁኔታ ተከብረዋል።

በክብረበዓሉ ላይ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የሚገኙ የኢ.ፈ.ዴ.ሪ.መከላኪያ ሰራዊት ምስራቅ እዝ አመራርና የጦር ሰራዊት መኳንትት አባላት፤የኢ.ሶ.ክ.መ.ልዩ ኃይል ከፍተኛ አመራርና የሰራዊቱ መኳንቶች አባላት፤እንድሁም የተለያዩ የክልሉ ጸጠታ አካላት ከፍተኛ አመራር አካላት፤ የክልሉ ፖሊስ ሰራዊት አባላት እንድሁም ሌሎች ጥሪ የተደረግላቸው ክቡር እንግዶችም ተገኝቷል።

በተጨማሪም የኢ.ፈ.ዴ.ሪ.ቤሔራዊ መከላኪያ ሰራዊት አባላት በክልሉ ፖሊስ ማርሽ ባንድ ተጅቦ በጅግጅጋ ከተማ በአማረ መልኩ የእግር ጉዞ ያደረገ ሲሆን የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ቦንድ ገዠም አከናውነዋል።

በበዓሉ መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የጅግጅጋ ከተማ አስተዳደር ካንቲባ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አብዱልአዚዝ ማሀድ  ኢ.ፈ.ዴ.ሪ.መከላኪያ ሰራዊት በዓል ቀን በኢትዮጵያ ሶማሊ ክልል  ርዕሰመዲና  በጅግጅገጋ ተከማ ለ7ተኛ ጊዜ በእንዲሁ በአማረ ሁኔታ በማክበሩ በጣም ደስተኛ ከመሆናቸው ባሻገር፤ቤሔራዊ መከላኪያ ሰራዊት አባላቱ ከኢትዮጵያ ሶማሊ ክልል ፖሊስ አካላት ጋር በመሆን የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ቦንድ መግዛታቸው የሀገራችን ቤሔራዊ መግባባትና የህዝብ ለህዝብ ትስስርን የበለጠ ያጠናክራል ብሏል።

 በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሺኔር  ፈርሃን ጣሂር የክብረ በዓሉ አስፈላግነትና አላማዎቹን እንዲሁም የሀገር መከላኪያ ሰራዊቱና የክልሉ ፀጥታ ሀይሎች ያስመዘገቡትን ስኬቶችና ድሎች አብራርቷል፡፡ ቤሔራዊር መከላኪያ ሰራዊቱ በሀገራችን አስተማማኝ ሰላም እንዲሰፍንና በታላቁ የህዳሴ ግድባችን የአንበሳ ድርሻቸውን ላበረከቱት አስተዋፆ ኮሚሺኔሩ የላቀ ምስጋናቸዉን አቅርቦዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ  የኢ.ፈ.ደ.ሪ.መከላኪያ ሰራዊት 38ኛ ክፍለ ጦር አዛዥ ኮረኔል ሀይሌ ተስፋዬ በበኩላቸው የሀገር መከላኪያ ሰራዊቱ ያስመዘገቡትን ስኬቶችና ድሎች በሀገሪቷ ሰለም በመስፈን እንዲሁም በጎረቤት ሀገራት ሰላምን ላበረከቱት ትልቅ አስተዋፆ በክብረ በዓሉ ላይ አብራርቶ ገልፀዋል፡፡አያይዞም ኮረኔሉ በሀገር መከላኪያ ሰራዊቱ  የተመዘገበዉን ስኬትና ድሎች በእጥፍ ድርብ በማጠፍ ቀጣይነታቸዉንም እንደሚያረጋግጡ ኣክሎ ገልፀዋል፡፡

በመጨራሻም የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት የፀጥታና ፍትህ አስተዳድር ቢሮ ም/ሃላፊ አቶ አህመድ መሀሙድ አህመድ በክብረ በዓሉ ስነ-ስርዓት ላይ  በመጨረሾቹ አመታት በክልሉ ያሉት የተለያዩ የፀጥታ ሃይሎችና ፖሊስ አካለት   በክልሉ ሰላም እንዲሰፍን እንዲሁም ለሀገሪቷ ያስመዘገቡትን የሰላም ስኬቶችን አብራርቷል፡፡ የተመዘገበው ድሎች ቀጣይነት እንዲኖር ለታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ በራሳችን አቅም ከዳር ለማድረስ የድርሻቸዉን እንዲወጡ ጥሪያቸዉን አስተላልፏል፡፡