የኢ.ሶ.ክ.መ.ፕሬዝዳንት አቶ አብዲ መሀሙድ በጅግጅጋ ከተማ በ398 ሚልዮን ብር የተገነባ ዘመናዊ የእስፋልት መንገድ አስመርቋል

ጅግጅጋ (cakaaranews)መክሰኞ፤ የካቲት 20/2010ዓ.ም. በጅግጅጋ ከተማ በ398 ሚልዮን ብር  የተገነባው የቆረሄይ ጎዳና ዘመናዊ የእስፋልት መንገድ ግንባታው ተጠናቆ የክልሉና የከተማ አስተዳደሩ የስራ ሀላፊዎች እንዲሁም የጅግጅጋ ከተማ ነዋሪዎች በተገኙበት በትላንት እለት በኢትየጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት ፕሬዝዳንት በክቡር አብዲ መሀሙድ ኡመር ተመርቋል፡፡

የኢትየጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አብዲ መሀሙድ ኡመር ግንባታው ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ለአገልግሎት የበቃው፤ የቆረሄይ ጎዳና ዘመናዊ የእስፋልት መንገድ ቀደም ብሎ በከተማው የነበረው የመንገድ መሰረተ ልማት ችግሮችን እንደሚቀርፍና በቆረሄይ ጎዳና የእስፋልት መንገድ ላይ የተገነበው ትልቁ ድልድይ ከዚህ ቀደም ድልድይ ባለመኖሩ በ05፣09፤17 እና 18 ቀበለዎች የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች በእለተ እለት እንቅስቃሴያቸውና በከተማው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ስራዎች ላይ አሉታዊ ተፅእኖ ሲያሳድር መቆየቱንና መንገዱን የተገነባበት አከባቢ ጠባብና አስቸጋሪ በመሆኑ ምክያት የመንገዱ ግንባታ ለሁለት አመታት እንድፈጀው አደርጓል ብሏል ክቡር ፕሬዝዳንቱ።

አያይዞም መንገዱ ባላሁለት ሳይት ሆኖ በአንደ ስድስት ተሽከርካሪዎች ማስተናገድ የሚችል ከመሆኑ በዘለለ ስፋቱ 30ሜትር እንደሆነና ከአሁን በፊት በከተማው የመንገድ መስረተ ልማት በኩል ይገጥማቸው የነበረው ችግሮች እንደሚቀርፍም ፕሬዝዳንት አብዲ ገልጿል፡፡

በሌላ በኩል በመንገዱ ምርቃት ስነ-ስርዓት ላይ የተገኙት የጅግጅጋ ከተማ ነዋሪዎች በበኩላቸው በክልሉ መንግስት የተገነባላቸው አስፋል መንገድና  ዘመናዊ ድልድይ  ለአገልግሎት ማብቃቱን የተሰማቸዉን ደስታ በመግለፅ ለክልሉ መንግስትና ለክቡር ፕሬዝዳንቱም የላቀ ምስጋናቸዉን አቀርበዋል፡፡

 

በተመሳሳይም ዘመናዊ ድልድይና አስፋልት መንገዱ በ398 ሚልዮን ብር ውጭ የተደረገበት ሲሆን ለከተማው እድገትና ውበትም ከፍተኛ ሚና እንደምጫወት ተገልጿል።