በውጭ ሀገር የሚኖሩ የኢ.ሶ.ክ. የፋፈን ዞን ተወላጆች 20ኛው የኢሶህዴፓ የምስረታ በዓልን አስመልክቶ በደማቅ ሁኔታ አክብሯል፡፡

ሚኒሶታ(cakaaranews)ሀሙስ 14, መጋቢት 2010. በሀገረ አሜሪካ በሚኒሶታ ግዛት የሚኖሩት የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የፋፈን ዞን ተወላጆች በአይነቱ ለየት ያለ 20ኛው የኢሶህዴፓ ምስረታ በዓልን አስመልክቶ በደማቅ ስነ-ስርዓት በሚኒሶታ ከተማ አክብሯል፡፡

በመሆኑም በስነ-ስርዓቱ ላይ በርካታ የክልሉ ተወላጆች ከተለያዩ የህብረተሰቡ ክፍሎች የተወጣጡ የሃይማኖት አባቶች፣ እናቶችና ወጣቶች እንድሁም በሀገረ አሜሪካ በሚኒሶታ ግዛት የሚኖሩት የክልሉ ተወላጆች በተለይም የፋፈን ዞን ተወላጅ የሆኑት ተገኝቷል፡፡ የክልሉ ተወላጆችም በዓሉን  በተለያዩ ሙዚቃዎችና የባህላዊ ዘፈኖችን ታጅቦ 20ኛው የኢሶህዴፓ ምስረታ በዓልን በደማቅ ሁኔታ አክብሯል፡፡ 

ይህ በእንዲህ እንዳለ የሃይማኖት አባቶቹና የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የዲያስፖራ ኮሚኒቲ አመራር አካላት   በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የተመዘገቡትን ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎችን በመብራረት እንዲሁም ድርጅቱ የተጎናፀፋቸው የልማት ስኬቶችን በማድነቅ በክብረ በዓሉ ላይ አስገንዝቧል፡፡ አያይዞም በመጨረሾቹ አስርተ ዓመታት የክልሉ መንግስት በተለያዩ ዘርፎች ያስመዘገባቸውን ውጤቶች ማለትም በኢኮኖሚያዊ፤ በማህበራዊ፤ በፖለትካዊና እንዲሁም በፍትህ ፤በዴሞክራሲና የመልካም አስተዳደር ዘርፎች ያስመዘገባቸውን ውጤቶች በስነ-ስርዓቱ ላይ ሪፓርት አቅርቧል፡፡

 

በክልሉ መንግስት የተከናወኑትን የልማት ስራዎች በግብርናዉ  መስክ፣ በአርብቶአደሩናከፊልአርብቶአደሩንበመንደርማሰባሰብስራበመሰረተልማትዘርፍየተመዘገቡውጤቶች እንደ መንገድ፣ በማህበራዊ ዘርፎች የተገኙት ውጤቶች እንደ ትምህርትጤናየንፁህ መጠጥ ዉሃአቅርቦት፣ የመብራትንና የስልክ አገልግሎቶችን አያይዞም በሀገረ አሜሪካ በሚኒሶታ ግዛት የሚኖሩት የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል  ተወላጆች ገለጿል፡፡  

በመጨረሻም ዲያስፖራ አባላቱ ከክልሉ መንግስትና ከመሪው ድርጅት ከኢሶህዴፓ ጎን ቆመው የድርሻቸዉን እንደሚወጡ  ቃል ገብቷል፡፡