ክቡር ፕሬዝዳንት አብዲ መሀሙድ በስልክ የተካፈሉበት 20ኛው የኢሶህዴፓ ምስረታ በዓል በሳውዲ አረብያ በደማቅ ስነ-ስርዓት ተክብሯል

ሪያድ(cakaaranews)ቅዳሜ ፤መጋቢት 22 2010. በሳውዲ አረብያ የኢትዮጵያ ባላሙስልጣን አምባሰደር  አሚን አብዲቃድር፣ በሳውዲ አረብያ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የዲያስፖራ ኮሚኒቲ አመራር አካላትና የተለያዩ የክልሉ ተወላጅ ህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበትና በአይነቱ ለየት ያለ ሥነ-ስርዓት በማዘጋጀት 20ኛው የኢሶህዴፓ ምስረታ በዓልን  በሪያድ ከተማ በደማቅ ሁኔታ አክብሯል፡፡

በተያያዜም ባለፉት አመታት በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የተመዘገቡትን ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎች ማለትም፣ በግብርና፣ በአርብቶአደርናከፊልአርሶአደር፤በመንደርማሰባሰብበመሰረተልማትዘርፍእንደ መንገዶች፤ውሃ እንድሁም በማህበራዊ ዘርፎች እንደ ትምህርትጤናየንፁህ መጠጥ ዉሃአቅርቦት፣ የመብራትንና የስልክ አገልግሎቶችን፣ የፍትህ ፤የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታና የመልካም አስተዳደር ዘርፎች ያስመዘገባቸውን ውጤቶች እንዲሁም በውጭም በሀገር ውስጥም የህዝብ ለህዝብ ትስስር ስራዎች ተጨባጭና አመርቂ ስኬቶች መጎናፀፉን  የኢ.ሶ.ክ ፕሬዝዳንት ክቡር አብዲ መሀሙድ ኡመር  በስነ-ስርዓቱ ለይ  ቀጥታ በስልክ ተካፍሎ መብራርያ መስጠታቸውን የኢ.ሶ.ክ.መ የዲያስፖራ መስተባበርያ ቢሮ ሀላፊና የፕሬዝዳንቱ የህዝብ ቅሬታ ዘርፍ አማካሪ  አቶ አብዲረዛቅ ሰሀኔ ገልጿል፡፡    

ይህ በእንዲህ እንዳለ ክቡር ፕሬዝዳንቱ የክልሉ ተወላጅ ሴቶች በሁሉም ዘርፍ ከክልሉ መንግስት ጎን ቆመው እያበረከቱ ያለዉን አስተዋፀኦና የበኩላቸዉን ድርሻ በማውጣታቸውን እጅግ በማመስገን እና በማድነቅ እንዲሁም በሌላው ዓለም ሀገራት የሚኖሩትን የክልሉ ተወላጅ ማህበረሰብ ባሉበት ቦታ ሁሉ የተለያዩ የሞያ ስራዎች ልምድ  እንዲቀስሙና እውቀት እንዲካበቱ ጥሪያቸዉን ማቅረቡን አቶ አብዲረዛቅ ሰሀኔ አክሎ ገልጿል፡፡ 

አያይዞም ክቡር ፕሬዝዳንቱ  በሳውዲ አረብያ የሚኖሩ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ተወላጆችና በሌሎች የዓለም ሀገራት ያሉት የክልሉ ተወላጆች ሁሌም ከክልሉ መንግስትና ከኢሶህዴፓ ድርጅት ጎን ቆመው እያበረከቱ ያለዉን አስተዋፆና ድጋፍ በማመስገን በሳውዲ አረብያ የኢትዮጵያ ባላሙሉ ስልጣን አምባሰደር  አሚን አብዲቃድር በሳውዲ አረብያ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ዲያስፖራ ኮሚኒቲ አመራር አካላትና አባላት ጎን ቆመው እየሰሩ  ያለዉን የዲፕለማሲ ስራዎች በማከናወናቸው የላቀ ምስጋናቸዉን አቅርቧል፡፡     

በመጨረሻም በሳውዲ አረቢያ ያሉት የዲያስፖራ ኮሚኒቲ አካለት ከክልሉ መንግስትና ከመሪው ኢሶህዴፓ ድርጅት ጎን ቆመው የበኩላቸዉን ድርሻ እንደሚወጡ ተናግረዋል፡፡