የኢ.ሶ.ክ.መ.የስነ ምግባርና ፀረ ሙሲና ኮሚሽን በክልል መ/ቤቶች የስነ ምግባር ኮሚቴ አባላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጣና ሰጥቷል

ጅግጅጋ(cakaaranews)ቅዳሜ መጋቢት 22/2010ዓ.ም. የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ስነ ምግባርና ፀረ ሙሲና ኮሚሽን ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ስነ ምግባርና ፀረ ሙሲና ኮሚሽን ጋር በመተባበር በክልል መ/ቤቶች የሚሰሩ የፀረ ሙሲና ኮሚቴ አባላት በጅግጅጋ ከተማ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል፡፡

በመድረኩ መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ስነ ምግባርና ፀረ ሙሲና ኮሚሽን ኮሚሽኔር አቶ መሀሙድ አብዱልቃድር መሀሙድ በአሁኑ ወቅት በክልሉ እየተከናወኑ ባሉ ዘርፈ-ብዙ የመሠረተ ልማት፤የመልካም አስተዳደርና የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ስራዎች ይበልጥ ለማጠናከርና በሀገሪቱና ብሎም በክልሉ መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ከመሆኑ ባሻገር በልማት ጉዞኣችን ላይ ትልቅ መሰናክል የሆነውን ሙስናና ከሙስና ጋር ተያያዠነት ያላቸው የፀረ ልማት ልማዶች የሚንከላከልበት ዘዴዎች እንድሁም የሙስና ምንነትና ሙስና በሀገር ግንባታ ላይ ሊያሰከትል የሚችሉ አደጋዎች አስመልክቶ የመድረኩ ዋና ዋና አጀንዳዎች መሆናቸውን አብራርቷል፡፡

የሙስና ወንጀሎችን ከመከላከል ረገድ፤ሙስና እንደማንኛውም ወንጀልና አደጋ ለመከላከል ተግባር ከመሆኑ በዘለለ በዋነኝነት ግን ሙስና ልዩ ከሚደርጉ ባህሪያት መካከል የብልሹ አሰራር ወንጀሎችና በሀገር ሀብት ላይ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ኪሳራ ሊያመጡ የሚችሉ ተግባራት ሲሆኑ እነዚህና መሰል አጸያፊ ድርግቶች ለመቀነስና ለማስቀረትም  በሚያስችል መልኩ የሙስና ችግሮች ምንጭ የማድረቅ ስራዎች ይጠብቅብናል ብሏል ኮሚኝኔሩ፡፡በተያያዜም  አጠቃላይ ከሙስና ትርጉም ጀምሮ በተቋማት ውስጥ ሙስና ተግባራት ቢከሰቱ በተቋሙና በሀገር ልማትም ሊሚያስከትለው የሚችሉ ጉዳቶችም በሰፊው ማብራርያ ሰጥተውበት፤የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ስነ ምግባርና ፀረ ሙሲና ኮሚሽንበነዚህ ጉዳዮች ዙሪያ ምን እንደሚመስሉ፤ሙስና ከመዋጋት አንፃር የተሰሩ ስራዎች እንድሁም የተቋሙ ነባራዊ ሁኔታ የሚዳስስ ጥናታዊ ሪፖርትም ኮሚሽኔር መሀሙድ አቀርቧል፡፡

አያይዞም  በግንዛቤ ማስጨበጫው ላይ የተገኙት የክልሉ ፀረ ሙስናና ስነ ምግባር ኮሚቴ አባላቱ ከስልጠናው ከአሁን በፊት በሙስና አደጋዎች ዙሪያ ያልነበራቸው ጥሩ አመለካከትና እውቀትም እንደሚያዳብሩና ለሀገር ልማት ብቁ ዜጎች እንደሚሆኑም ሙሉ እምነት አለኝ ብሏል አቶ መሀሙድ አብድቃድር፡፡