በግብርናና በምግብ ዋስትና አመርቂ ውጤቶች ያስመዘገቡ ሞዴል ሴት አርሶ አደሮች በድሬደዋ ከተማ ሽልማት ተበረከተላቸው

ድሬደዋ(Cakaaranews) ሰኞመጋቢት 24/2010በግብርናዘርፍተሰማርተውሃብትያፈሩና ከኢትዮጵያ ሶማሌ ፤ ከድሬደዋ መስተዳድርና ከሐረሪ ክልሎችና የተወጣጡ  ሞዴል ሴት አርሶአደሮች በድሬደዋ ከተማ ተሸለሙ።

የሽልማት ስነ-ስርዓቱ በጋራ ያዘጋጁት የኢ.ፌ.ደ.ሪ. ግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስቲሪ፣ ኦክስፎምና ሴራ ሀገር በቀል መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በጋራ በመተባበር ስሆን ይህ ሽልማት መድረክ በየ አመት የሚደረግና ዋና አላማው ደግሞ ሴት አርሶ አደሮችን ለማበረታታት እንድሁም በእነርሱአርዓያየሚሆኑአርሶአደሮች የመሪነትሚና እንድኖራቸው ከግምት በማስገበት ነው፡፡

 በተጨማሪም በመድረኩ መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የድሬደዋ መስተዳድር የህብረት ስራ ማህበራት ኤጄንሲ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ገበየው ጥላሁን  በመጀመሪያ ከድሬደዋ መስተዳድር፣ ከሀረሪ ክልልና ከኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የተወጣጡ  ሞዴል ሴት አርሶአደሮችን የእንኳ ደህና መጣቹ መልዕክታቸዉን በማስተላለፍ ሞዴል ሴት አርሶአደሮችበግብርናና በምግብ ዋስትናዘርፉባስመዘገቡትየላቀአፈጻጸምና ላበረከቱት አስተዋጸኦ በድህነት ለይ የተጀመረዉን ትግል ማሰያ መሆናቸውን  ገልጿል፡፡ 

 

በመሆኑም ከኢትዮጵያ ሶማሌ፤ከድሬደዋ መስተዳድርና ከሀረሪ ክልሎች የተወጣጡ  ሞዴል ሴት አርሶአደሮች በግብርናው ዘርፍ ላስመዘገቡት ስኬቶች አስመልክቶ የገንዘብና የእውቅና ሰርተፊኬት ተበረክቶላቸዋል፡፡ 

በአጠቃላይ በግብርናው ዘርፍ አመርቂ ውጤቶች ያስመዘገቡ ሞዴል ሴት አርሶአደሮችበመንግስት ደረጃ በመሸለማቸውየተሰማቸዉን ደስታ በመግለፅ ሽልማቱ የበለጠ እንደሚያበረታታቸውም አብራርተዋል፡፡