የኢፈዴሪ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ሁለተኛው አስቹኳይ ስብሰባቸው ዶር አቢይ አህመድ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር አደርጎ ሰይሟል

አዲስ አበባ(Cakaaranews)ሰኞ፤ መጋቢት 24፣ 2010 ዓ.ም.የኢህአዴግ ምክርቤት ዶር አቢይ አህመድ የድርጅቱ ሊቀመንበር አደርጎ መምረጣቸውን ተከትሎ የኢህአዴግ ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽ/ቤት ሃላፊ ክቡር አቶ ሽፈራው ሽጉጤ የዶር አቢይ አህመድ ህይወት ታሪክና የስራ ልምድ  ለኢፈዴሪ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ሁለተኛው የአስቹኳይ ስብሰባ በማቅረብና ዶር አቢይ አህመድ ለሀገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትርነት እንድሰየሙ ከጠየቁ በሆላ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላቱ  ዶር አቢይ አህመድ የኢፈዴሪ ጠቅላይ ሚንስትር አደርጎ ሰይሟል።                                         

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የነበረው ቆይታ እንደተጠናቀቀም ለአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አቀባበል ስነ ስርዓት በጠቅላይ ሚንስትር ጽህፈት ቤት ተካሂዷል።

በአቀባበሉ ላይም የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝና ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናትን ጨምሮ የጠቅላይ ሚንስትሩ ባለቤት ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸውም ተገኝተዋል።የቀድሞው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በፅህፈት ቤቱ ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ቢሮዎችን አዘዋውረው አስጎብኝተዋቸዋል።

የቀድሞው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግርም፥ በቀጣይ ጊዜያት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን በሙሉ ልብ እንደሚደግፉ አስታውቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትርነት ቀላል የሚባል ኃላፊነት አይደለም ያሉት የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ መሰዋዕትነትን ለመክፈል ለተዘጋጀ ሰው ግን በቀላሉ ማለፍ ይቻላል ብለዋል።

ዋናው ኃላፊነት የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ቢሆንም፤ አስፈላጊውን ትብብር እና እገዛ ግን በማንኛውም ጊዜ ለመስጠት ዝግጁ መሆናቸውን የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ተናግረዋል።

አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በበኩላቸው፥ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ይህችን ሀገር ለመምራት ከባድ የሃላፊነት ጊዜን አሳልፈዋል፤ ለዚህም ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል።

አቶ ኃይለማርያም ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር በማድረግም አርአያ መሆን እንደቻሉ የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ፥ እሳቸውም በዚሁ መልኩ የስልጣን ሽግግር ማድረግ እንደሚፈልጉ ገልፀዋል።

ህዝብና መንግስት የሰጣቸውን ኃላፊነት በአግባቡ ለመወጣት እንደሚሰሩ ነው የገለፁት።

በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ተግኝተው ስራ መጀመራቸውን ተከትሎም የቀድሞው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ አሸኛኘት ተደርጎላቸዋል።