የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አብዲ መሀሙድ ወደ ክልሉ መዲና ተመለሱ

ጅግጅጋ(Cakaaranews)ማክሰኞ፤መጋቢት 25/2010ዓም.የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አብዲ መሀሙድ ኡመርና የክልሉ ም/ቤት አፈጉባኤና የኢ.ሶ.ህ.ዴ.ፓ.ሊቀመንበር አቶ መሀመድረሺድ ኢሳቅ በአዲሱ ጠቅላይ ሚንስትር የሹመት ሥነ-ስርዓት ላይ የነበራቸው ተሳትፎና በኢፈዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶር አብይ አህመድ በብሔራዊ ቤተመንግስት የተደረገላቸው ልዩ የእራት ግብዣ ከተካፈሉ በኋላ ወደ ክልሉ መዲና የተመለሱ ሲሆን ዛሬ ከሰዓት በኋላ ጅግጅጋ ከተማ በዝናባማና ምቹ ኣየር በላበት ወቅት ላይ ነው የገቡት።