የኢ.ሶ.ክ.መ. የስነዜጋና ስነ-ምግባር መምህራን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እተሰጠ ይገኛል

ጅግጅጋ(cakaaranews) ቅዳሜ፤ሚያዝያ 13/2010ዓም. ኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት  ትምህርትቤቶችየሚሰሩሁሉንም የስነ-ዜጋና ስነ-ምግባር መምህራን ሞያቸዉን ከፍ ለማድረግና ጥሩ ክህሎት እንዲኖራቸው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በዛሬ እለት በይፋጀምሯል:: ስልጠናው በ7 የክልሉ ከተሞች ማለትም በጅጅጋ፣ በደገህቡር፣ በቀብሪዳሀር፣ በጎዴ፣ በዋርዴር፣ በሀርጌሌና በፍልቱ እየተሰጠና ከ3900 በላይ መምህራንን በማሳተፍ ለይ እንደምገኝም የክልሉ አስታውቋል፡፡

ስልጠናው ከሚሰጥባቸው ከተሞች አንዱ ጅጅጋ ሲሆን በስልጠናው መክፈቻ ስነ-ስርዓት ላይ የኢ.ሶ.ክ.መ. ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ኢብራህም አደን መሀድ የስልጠናዉን አስፈላግነትና ጠቀሜታ እንዲሁም የስነዜጋና ስነ-ምግባር ትምህርት ለህብረተሰቡ ያለዉን ፋይዳ ለሰልጣኞቹ መምህራን  አብራርተዋል፡፡

በክልሉ ትምህርት በሮ የሚሰሩ ሁሉም መምህራንና ሰራተኞች በክልሉ መንግስት በታቀደዉን የትምህርት ልማት ግቦችን ከዳር ለማድረስና የትምህርት ጥራትን ለማጎልበት ትልቅ ሀላፍነት እንዳለባቸው ቢሮ ሀላፊው አሳብቧል፡፡ ከዚህው ጋር ተያይዞ ሰልጣኝ መምህራኖቹ በተሰማሩበት የትምህርት መስክ ጥራት ያላቸዉን ና ብቁ ተማሪዎቹን ለማፍራት ጥራት ያለው ትምህርት ለተማሪዎቹ እንዲያደርሱና  የበኩላቸዉን ድርሻ እንዲወጡ ቢሮ ሀላፊው ከአደራ ጭምር አሳስቧል፡፡

በሌላ በኩል የክልሉ ትምህርት ቢሮ የስነ-ዜጋና ስነ-ምግባር ደይሬክቶሬት ደይሬክተር ወ/ሮ ፈርህያ አብዱላሂ ከሊፍ የግንዛቤው ማስጨበጫ ስልጠና ለሰልጣኞቹ ትልቅ ፋይዳና ጠቀሜታ እንዳለው በመናገር፤ ስልጠናው በ7 የክልሉ ከተሞች ከ3900 በላይ መምህራንን በማሳተፍ ላይ እንደምገኝ ደይሬክተሯ ተናግረዋል፡፡   

በአጠቃላይ ይህ አይነቱ ስልጠና የመጀመሪያዉና በሀገር ኣቀፍ ደረጃ በተመሳሳይ መልኩ የስነ-ዜጋና ስነ-ምግባር መምህራንን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየተሰጠ ላይ ይገኛል፡፡