ዝናብ መልካም ቱራፋቶች እንዳለው ሁሉ ከጥንቃቄ ካልታከለበት የሚያስከትለው ጉዳትም ከፍተኛ መሆኑ ይታወቃል።

ጅግጅጋ (cakaaranews)እሁድ፤ሚያዝያ 14/2010ዓም.እንደምታወቀው በቀንድ አፍሪካ በተለይም በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የሚኖሩ የሶማሌ ህብረተሰብ በአመት ውይም በሁለት አመቱ አንዴ በድርቅ ይጠቁ ነበር። በዚህም በማህበረሰብ እውቀት ማነስ፤ግንዛቤ አለመስጠቱና በአለም እየተከሰተ ያለው የአየር ንብረት ለውጥ  ችግሮች  በህብረተሰቡ ዘንድ መገመት ስለማይቻል በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል  አከባቢ የሚኖሩ የማህበረሰብ ክፍሎች በአመት ውስጥ የሰውና በእንስሳት ህይወት ለከፋ ድርቅ ይጋለጥ ነበር።

በመሆኑም ለ30 አመታት ያህል በክልሉ አከባቢዎች ያልጣለ ዝናብና በአሁኑ ወቅት በክልሉ አከባቢዎች  እየጣለ ያለው ከባድ ዝናብን የክልሉ መንግስት ቀደብ ብሎ ብያስጠነቀቅም የዝናቡ ክብደት ያስከተለው  የጎርፍ ማጥለቅለጥ በሰውና በንብረትም ጉዳት ማስከተሉን የክልሉ መንግስት አስታውቋል።የዝናቡ ጎርፍ ደግሞ በዋቢ ሸቤሌ ዳርቻ አከባቢ የሚገኙ ወረዳዎች እንደ ምስራቅ ኢሜይ፤ቀላፎና ሙስተሂል ለችግሩ ተጋላጭ ሆነው ነገር ግን አስቹኳይ እርዳታ ለሚያስፈልጉና ለችግሩ ሰለባ ከሆኑ ወረዳዎች መካከል ፌርፌር፤ጎዴና በፋፋን ወንዝ ዳር የሚያገኙ አንድ አንድ የጅግጅጋ ከተማ ሰፈሮች መሆናቸውን የክልሉ አደጋ መከላከልና ዝግጁነት ቢሮ አስታውቋል።

በተጨማሪም የክልሉ መንግስት በፋፈን ወንዝ ጎርፍ የተጎዱ የጅግጅጋ ከተማ ቤተሰቦች በተደጋጋሚ የቤት ቁሳቁስና የተለያዩ የምግብ አይነቶች ያደረሰ ሲሆን አሁንም በጎርፉ የተጎዱ አከባቢዎችም ከችግሩ ለማዳን በርካታ የቤት ቁሳቁስና የተለያዩ የምግብ አይነቶች  የያዙ የእርደታ መኪናዎችን መሰማራቱን የክልሉ አደጋ መከላከልና ዝግጁነት ቢሮ አስረድቷል።አያይዞም በክልሉ የተሰሩ ትላልቅ ፤መካከለኛና ትናንሽ አፈር ዳሞች እንድሁም በክልሉ በአጭር ጊዜ ውስጥ የተሰሩ ቤርካዎች መሟላታቸውን ተከትሎ ህዝቡ ለመስኖ መጠቀም እንዳለበትም ቢሮው አስረድቷል። በተጨማሪም የክልሉ መንግስት፤ ህብረተሰቡ ለዝናብ ውሃን ለመስኖና ለውሃ ማቆሮች እንድጠቀሙና ከዝናቡ ጎርፍ እንድጠነቀቁ አሳስበዋል።

በመጨረሻም የክልሉ አደጋ መከላከልና ዝግጁነት ቢሮ በአጠቃላይ የክልሉ መንግስታዊና መንግታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፤የፌዴራል አደጋ መከላከል ባላድርሻ አካላት፤በፌደራልና ክልሉ የሚሰሩ ለጋሽ ድርጅቶችና ለሚመለከተው የግልና የመንግስት አካላት ሁሉ በክልሉ ትላልቅ ወንዞች አከባቢዎች ለሚገኙና በጎርፉ የተጎዱ ዜጎች ለሚደረግለት ድጋፍና እርዳታ የበኩላቸ ው ድርሻ እንድወጡ ጥሪ አቀርበዋል።