የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስትና ኢህሶዴፓ አዳዲስ የካቢኔ ሹመትና ሽግሽግ አጸደቀ

ጅግጅጋ(Cakaaranews)ሰኞ፤ሚያዝያ 15/2010ዓ.ም.የኢትዮጵያ ሶማሌ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ  ማዕከላዊ ኮሚቴ በትላንትናና ዛሬ ባካሄዱት ስብሰባ በክልሉ መስሪያቤቶች ከፍተኛ አመራር አካላትና በአንዳንድ ዞኖች አመራርም አዳዲስ የካቢኔ ሹመትና  ሽግሽግ አደረጉ።

መድረኩን የመሩት ኢህሶዴፓ ሊቀመንበር አቶ መሀመድረሺድ ኢሳቅና የኢሶህዴፓ ም/ሊቀመንበርና የክልሉ መንግስት ፕሬዝዳንት  ክቡር አቶ አብዲ መሀሙድ  ኡመር  ሲሆኑ ም/ቤቱ አዳዲስ የካቢኔ ሹመትና ሽግሽግ በሙሉድምጽ አጽድቀዋል።

አዳዲስ ሹመቶችና ሽግሽግን እንደሚከተለው:-

1.      ወ/ሮ ፈርቱን አብዲ ማህዲ------የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ሀላፊ

2.     አቶ አህመድ አብዲ---- የውሃ ሀብት ቢሮ ሀላፊና ስራ የኢህሶዴፓ አስፈፃሚ አባል

3.     አቶ አብዲሀኪም ኢጋል---- የአርብቶ አደር ማህበረሰብ ልማት ፖሮጀክት ጽ/ቤት ሀላፊ የኢህሶዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል

4.     ወ/ሮ ሱኣድ አህመድ ፋረህ--------በነበሩበት

5.     አቶ ከደር አብዲ ኢስማእል-------- የኢ.ሶ.ህ.ዴ.ፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ፅ/ቤት ሀላፊ

6.   አቶ ሀምዲ አደን አብዲ-------የኢ.ሶ.ክ.መ ም/ፕሬዝዳንትና የክልሉ ጤና ቢሮ ሀላፊ

7.     አቶ ሱልጣን መሀመድ ሀሰን-----------  የስራ አስፈፃሚ አባልና የመስኖና ተፋሰስ ልማት ቢሮ ሃላፊ

8.     ወ/ሮ ማጂዳ መሀመድ--------የመስተዳደር ፅ/ቤት ሃላፊ

9.     አቶ ኡመር መሀመድ----------በነበሩበት

10.   አቶ ኢብራህም አሊ---------የሰይንስና ቴክኖሎጂ ቢሮ ሃላፊ

11.     አቶ ባሼ አብዲ እስማኢል--የሰይንስና ቴክኖሎጂ ም/ቢሮ ሃላፊ

12.    አቶ ፉኣድ ጃማ ወላቢ-----------የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሀላፊ

13.    አቶ መሀመድ ረቢዕ ሃጂ አብዲቃድር--------- ገቢዎች ባላስልጣን ዋና ስ/አስኪያጅ

14.   አቶ አብዲላሂ መሀመድ ገርቦ------------የአደጋ መከላኪያና  ዝግጁነት ቢሮ ሀላፊ

15.    አቶ ሃሩን ዩሱፍ አብዲ------ ንግድ፣ ትራንስፖረትና ኢንዱስትሪ ቢሮ ሀላፊ

16.   ወ/ሮ ረህማ መሀሙድ--------በነበሩበት

17.    አቶ አብዲመሀድ መሀመድ አባስ---------የእንስሳትና አርብቶኣደር ልማት ቢሮ ሀላፊ

18.   አቶ ጀማል ፋረህ ወርሞጌ----------የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ሀላፊ

19.   አቶ ኢብራህም አደን መሀድ--------በነበሩበት 

20.  አቶ አብዲጀማል አህመድ ቆለንቢ-------በነበረበት

21.    አቶ ጀማል ኢስማን ቆረኔ--------------የስራ አስፈፃሚ አባል

22.   አቶ መሀመድ ቢሌ ሀሰን----------------የቴክኒክ፣ ሞያና ትምህርት ስልጠና ቢሮ ሃላፊ

23.    ሲንጅነር አሰድ ኡመር------------በነበረበት

24.  አቶ ረሺድ ጃመእ ሼር---------- ምክትል ቢሮ ሀላፊ

25.   አቶ ሀሰን አደን ሀሰን----------ምክትል ቢሮ ሀላፊ

በዞን የተሾሙት እንደሚተከሉት ይሆናል፤

1.      አቶ አብዲአሲስ አህመድ ሀቢዬ-----------ቀድሞ የሸቤሌይ ወረዳ አስተዳዳሪ የነበሩት አሁን የቆረሄይ ዞን አስተዳዳሪ

2.     አቶ ሙሁመድ ሀሰን ሱፊ----------- ከደገህቡር ከተማ  ከንቲባነት ወደ  የጀረር ዞን አስተዳዳሪ

3.     አቶ ሀቢብ አደን----------ከወረዳ አስተዳደሪነት  ወደ ዞን አስተዳዳር ኃላፊነት  

4.     አቶ መሀመድ አሊ--------የፋፈን ዞን ትምህርት መመሪያ ኃላፊ የነበሩ  ወደ የዳዋ ዞን አስተዳድር ኃላፊ

ማሳሰቢያ፤ከዚህ ውጭ ያሉት አመራሮች በነበሩበት ቦታ የቀጠሉ ናቸው።