የኢ.ሶ.ክ.መ.ባህል ሳምንት በጅግጅጋ ከተማ በደማቅ ሁኔታ ተጀመረ

ጅግጅጋ(cakaaranews)ሀሙስ፤ሚያዝያ 18/2010ዓም. የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ባህል ሳምንት ለመጀመሪያ ጊዜ በክልል ደረጃ በባህልና ቱሪዝም ቢሮ አዘጋጅነት በክልሉ ርዕስመዲና በጅግጅጋ  ከተማ በደማቅ ሁኔታ ተጀመረ።በሥነ-ስርዓቱ ላይ ከ6ቱ ከተማ መስተዳደሮችና ከዞኖች የተወጣጡ ባህል ቡዱኖች በክልሉ ዋና ከተማ ጎዳናዎች በርካታ የሶማሌ ባህል ትርዕቶችና ባህላዊ ውዝዋዜዎችን በተለያዩ መንገዶች እያሳዩ ይገኛሉ።

በተጨማሪም የኢ.ሶ.ክ.መ.ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ፉኣድ አህመድ ጃማዓ እና የሳይንስና ቴክኖለጂ ም/ቢሮ ሃላፊና የቀድሞ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ባሼ አብዲ እስማኢል  በክልሉ ሚዲያ በጋራ ባነጋገሩት ወቅት የኢትዮጵያ ሶማሌ ብሔረሰብ ባህላዊ ቅርሶች ለማስተዋወቅና ባህላዊ ትውፋቶች ወደ ቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ በክልል ደረጃ የባህል ሳምንት ፌስትፋል ማዘጋጀቱን ወሰኝ ሚና እንዳለው አስታውቀዋል።አያይዞም የክልሉ ባህል ሳምንት ፌስትፋል ዋና አላማ በክልሉ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች የሚገኙየማይዳሰሱ ባህላዊ ቅርሶች ለማጥናት፤ለመንከባከብና ለማስተዋወቅ ከመሆኑ በተጨማሪ የክልሉ ዞኖች፤ወረዳዎችና ከተማ መስተዳደሮች የሚገኙ ባህል ቡዱኖች ለማስተሳሰር እንደሆነም ሃላፊዎቹ ገልጿል።

 የከተማ መስተዳደሮችና ወረዳዎች የተወጣጡ ባህል ቡዱኖች በክልል ደረጃ የብሔረሰቡ ባህል ሳምንትማዘጋጀቱና የተለያዩ የክልሉ ባህል እሴቶች እራሳቸው ባህላዊ ቅርሶችን መለዋወጣቸው እና ባህላቸው በአደባባይ በትዕይንት ማቅረባቸው ደስተኛ መሆናቸውን ለሚዲያ ተናገረዋል።

በተጨማሪም ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ በክልል ደረጃ የሚከበረው የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ባህል ሳምንት ለቀጣዩ ቀናት በክልሉ ሚዲና የተለያዩ የሶማሌ ባህላዊ ቅርሶች፤ባህላዊ ትርዕቶች በትላልቅ ጎዳናዎች እንደሚቀርቡና በፌስትፋሉ የሙዝየም ባህላዊ ቁሳቁሶችና የባህል ጥናታዊ ጽሁፎች በስምፖዝየም እንደምቀርቡና በጅግጅጋ ከተማ አከባቢዎች የሚገኙ የቱሪዝም መስህቦች እንደሚገኙም የኢ.ሶ.ክ.መ.ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስረድቷል።