በኢፈዴሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድና በኢሶክመ.ፕሬዝዳንትአቶ አብዲ መሀሙድ የሚመራ ከፍተኛ የመንግስት ልኳን ቡዱን ወደ ጅቡቲ አቀኑ

አዲስአበባ(Cakaaranews) ቅደሜ፤ሚያዝያ 20/2010ዓም.በኢፈዴሪ ጠቅላይ ሚንስትር ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድና በኢ.ሶ.ክ.መ.ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አብዲ መሀሙድ ኡመር የሚመራ የፈዴራልና የክልል መንግስታት ከፍተኛ ልኳን ቡዱን በዛሬ እለት ከሀገራችን ርዕሰመዲና ከአዲስ አበባ ወደ ጅቡቲ ሪፐብሊክ አመሩ።

ከልዑኳን ቡዱኑ መካከል የኢፈዴሪ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሃላፊ ሚንስትር አቶ አህመድ ሺዴ፤የኢ.ሶ.ክ.መ.ም/ቤተ አፈጉባኤ አቶ መሀመድረሺድ ኢሳቅ፤የኢ.ሶ.ክ.መ.የአርብቶ አደር ማህበረሰብ ልማት ፖሮጀክት ዋና አስተባባሪ አቶ አብዲሀኪም ኢጋል፤የውሃ ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ አህመድ አብዲ፤የኢ.ሶ.ክ.መ.ትምህርት ቢሮ ሃላፊ አቶ ኢብራህም አደም፤የድሬደዋ አስተዳደር ካንቲባ አቶ ኢብራህም ኡስማን እና የጠቅላይ ሚንስቴሩ ልዩ አማካሪ አምባሳደር መሀሙድ ዲሪር እንዲሁም የኢትዮጵያ ሶማሌ ሀገር ሽማግሎች ተወካይ የሆኑት ኡጋስ ሙስጠፌ መሀመድ ኢብራህም ይገኙበታሉ።

የኢፈዴሪ ጠቅላይ ሚንስተሩ ልዑኳን ቡዱን ከጀቡቲ መንግስት ከፍተኛ አመራር አካላት በተለያዩ የልማት ዘርፎችና bሁለትዮሽ ግንኙነት ዙሪያ እንደሚወያዩበት ይጠበቃል።