የኢ/ሶ/ክ/መ ፕሬዝዳንት ክቡር አብዲ መሀሙድ ልዑኳን ቡዱን ከጅቡቲ ወደ ክልሉ መዲና ተመለሱ

ጅግጅጋ(Cakaaranews) ሰኞ ፤ ሚያዝያ 22/2010 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አብዲ መሀሙድ ኡመር ከክልሉ ም/ቤት አፈጉባኤና የኢ.ሶ.ህ.ዴ.ፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽ/ቤት የድርጅት ጉዳዮች ዘርፍ ኃላፊ አቶ መሀመድረሺድ ኢሳቅ ጋር በመሆን የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ለመጀመሪያ ጊዜ በውጭ ሃገር ጉብኝት ወደ ጅቡቲ ሪፐብሊክ ያደረጉት የሁለት ቀናት የስራ ጎቡኝት ከተካፈሉ በኋላ ወደ ክልሉ ርዕሰ መዲና ወደ ጅግጅጋ ተመለሱ

ከልዑኳን ቡዱኑ መካከል የኢ.ሶ.ክ.መ የአርብቶ አደር ማህበረሰብ ልማት ፖሮጀክት ዋና አስተባባሪ አቶ አብዲሀኪም ኢጋል ፣ የክልሉ የውሃ ሀብት ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ አህመድ አብዲ ፣ የትምህርት ቢሮ ኃላፊአቶ ኢብራህም አደም ፣ የኢትዮጵያ ሶማሌ ሀገር ሽማግሌዎች ተወካይ የሆኑት ኡጋስ ሙስጠፌ መሀመድ ኢብራህም ይገኙበታሉ። ፕሬዝዳንቱ እና ልዑኳን ቡድኑ  በአሁኑ ወቅት በክልሉ  ርዕሰ መዲና ወደሆነችው ጅግጅጋከተማ ተመልሰዋል።