በሺላቦ ወረዳ በዝቅተኛ ኑሮ ደረጃ የሚኖሩ አባወራዎች የመስረተ ልማት ተኮር እቅድ ተጠቃሚ ማድረጋቸውን ተገጸ

ሺላቦ(cakaaranews) ማክሰኞ᎓ሚያዝያ 23/2010ዓ.ም.በኢትዮጵያ ሶማሊ ክልል መንግስት በቆረሄይ ዞን ጸጥታ ዘርፍ ሃላፊና የሺላቦ ወረዳ አስተዳዳሪ የሚመራ ከፍተኛ የዞን ልዑኳን ቡዱን በሺላቦ ወረዳ በክልሉ መንግስት የታቀደለት የውሃ፤የግብርና፤የጤናና የትምህርት መስረተልማት ተኮር እቅድ ተግባራዊ ለማድረግ በወረዳው  የሚገኙና በዝቅተኛ ኑሮ ደረጃ የሚኖሩ የማህበረሰብ ክፍሎች የመስረተልማት ተኮር እቅድ ቀሳቁሶች ማከፋፈላቸውና ህብረተሰቡ ተጠቃሚ ማድረጋቸውን የሺላቦ ሊቀመንበር አቶ አብዲናስር ሙሁመድ ገልጸ።

በተጨማሪም ይህ የክልሉ የመስረተ ልማት ተኮር እቅድ የክልሉ አርብቶ አደር ማህበረሰብ ከቦታ ቦታ የሚንቀሳቀሱበት የአኗኗር ዘይቤ የሚቀይርበትና ህብረተሰቡ በምግብ ዋስትና ራሳቸው ለማስቻል  እንዲሁም የህብረተሰቡ ግንዛቤ በማሳደግ᎓ የክልሉ አርብቶ አደር ማህበረሰብን ወደ ከፍል አርሶ አደር የሚሸጋገርበት እና በፌዴራልና በክልሉ መንግስት በጋራና በተናጠል ከታቀዱት ትላልቅ የመስረተ ልማት እቅዶችና ስተራቴጂዎች አካል  ሲሆን በኢ.ሶ.ክ.በቆራሄይ ዞን ሺላቦ ወረዳ  የሚገኙና በዝቅተኛ ኑሮ ደረጃ የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች የዞኑ ዞኑ ጸጥታ ዘርፍ ሃላፊና ሺላቦ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ የሚመራ ልዑኳን ቡዱን ለማህበረሰቡ የመኖሪያቤት ᎓የመኖሪያቤት ማገልገያ ቁሳቁሶች፤ዘመናዊ  የእንስሳት እርባታ ማዕከላት ከነ-እንስሳቱ፤የታረሴ እርሻ እና ለረጅም ጊዜ ያህል የሚኖሩበት ሬሽን ተከፋፍሏል።

በሌላ በኩል በዞኑ የታቀደው የመስረተ ልማት ተኮር እቅድን አስመልኪቶ ለክልሉ ሚዲያ ማብራሪያ የሰጡት የቆራሄይ ዞን ጸጥታ ዘርፍ ሃላፊ አቶ መሀመድ አህመድ ኑር “ይህ እቅድ የማህበረሰቡ ኑሮ ለማሻሻልና ደህነትን ለመታገል በሁሉም የመስረተልማት ዘርፎች የታቀደ ሲሆን  በሺላቦ ወረዳ በዝቅተኛ ኑሮ ደረጃ የሚኖሩ ቤተሰብ አካላት ተጠቃሚ የሚናደርግበት ሲሆን በአርብቶ አደርነት ሲኖሩ የነበሩ ማህበረሰብን ወደ ተረጋገ ኑሮ ለመለወጥ ወሰኝ ተግባራት ተሰርተዋል” ብሏል።

የሺላቦ ወረዳ  ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብዲናስር ሙሀመድ አብዲሌ  በበኩላቸው“የአርብቶ አደሩ ማህበረሰብ ወደ ከፍል አርብቶ አደርነት ለመለወጥ የወረዳው አመራሮች ከፍተኛ ጥረትና ርብርብ ካደረጉ በኋላ  በዝቅተኛ ኑሮ ደረጃ የሚኖሩ 42 እማ/አባ ወራዎች ተጠቃሚ ለማድረግ ለየአንዳንዱ ቤተሰብ መኖሪያቤት ᎓የመኖሪያቤት ማገልገያ ቁሳቁሶች፤ዘመናዊ  የእንስሳት እርባታ ማዕከላት ከነ-እንስሳቱ፤የታረሴ እርሻ እና ለወራት ያህል የሚኖሩበት የረሽን አይነቶች” ታድለዋል ብሏል ሊቀመንበሩ።ቀጣይ ጊዜያትም ይህ የልማት ስራዎች በወረዳው እንደሚከናወኑም ሊቀመንበሩ አክሏል።