በጅግጅጋ ከተማ ከወጣቶች ጋር የሚመክርበት መድረክ ተከሄዷል

ጅግጅጋ(cakaaranews)ዕሮብ᎓ሚያዝያ 24/2010ዓ.ም.በጅግጅጋ ከተማ የሚኖሩ ወጣቶች ያሳተፈ እና በክልሉ ሰላም፤ጸጥታ᎓ልማትና መልካም አስተዳደር ስራዎች የሚመክርበት መድረክ በጅግጅጋ ከተማ በሰይድ መሀመድ አደራሽ ተካሄደዋል።በምክክር መድረኩ ላይም የጅግጅጋ ከተማ አስተዳደር ካንቲባ እና ሌሎች የክልሉ መንግስት ከፍተኛ አመራር አካላት ተገኝተዋል።

ይህ አይነት መድረክ ከክልሉ ወጣቶች ጋር  ለማድረግ ሌሎች የተለያዩ  ፈር ቀዳጅ የሆኑ መድረኮች መነሻ በማድረግ የጅግጅጋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ኢብራህም መሀሙድ ሙባረክ ተናግረዋል። አያይዘውም ክቡር ከንቲባው ወጣቶቹ የክልሉ የነገ ተስፋ በመሆናቸው በክልሉ እየተከናወነ ያለውን የልማት ስራዎች ጉልህ ሚና እንዲኖራቸውና የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል። ሃገራችን ኢትዮጵያና የክልሉ መንግስታችን የወጣቶችን ልማት ቅድሚያ በመስጠት እንዲሁም ለወጣቶቹ የስራ እድል ፈጠራን በማመቻቸት ስራ አጥነትን ከመቀነስ  ድህነትን ከመዋጋት እና ሃገራችን መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሃገራት ተርታ ለማሰለፍ  የወጣቶች ሚና የላቀ መሆኑን  ከንቲባው አክሏል።

 

በሌላ በኩል በመድረኩ ላይ የተሳተፉት ወጣቶች የተሰማቸውን ደስታና ስሜት በማብራራት በመድረኩ ላይ የተለያዩ አጀንዳዎች እንደ ሰላምና ጸጥታ ፣ልማት መልካም አስተዳደር ዙሪያ በመወያየት በክልሉ እየተሰሩ ያሉ ዘርፈብዙ  የጸጥታ᎓የልማትና ዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡ ተናግረዋል።