በደናን ወረዳ በዝቅተኛ ኑሮ ደረጃ የሚኖሩ አባወራዎች የመንደር ማሰባሰብና የልማት ተኮር እቅዶች ተጠቃሚ ማድረጋቸውን ተገጸ

ደናን(cakaaranews)ዕሮብ᎓ሚያዝያ 24/2010ዓ.ም.የኢ.ሶ.ክ.መ. የመስረተልማት ተኮር እቅድ በ2010ዓ.ም. ሀገሪቱ ከደህነት ለማላቀቅና መካከለኛ የኢኮኖሚያሚ ገቢ ካላቸው ሀገራት ተርታ ለመሰለፍ የተነደፉ ስተራቴጂያዊ እቅዶች አንዱ ሲሆን  ይህ የክልሉ የመስረተ ልማት ተኮር እቅድ የክልሉ አርብቶ አደር ማህበረሰብ ከቦታ ቦታ የመዘዋወር አኗኗር ዘይቤ የሚቀይርበትና ህብረተሰቡ በምግብ ዋስትና ራሳቸው ለማስቻል  እንዲሁም የህብረተሰቡ ግንዛቤ በማሳደግ᎓ የክልሉ አርብቶ አደር ማህበረሰብን ወደ ከፍል አርሶ አደርነት ለማሸጋገር የተነደፉ ስተራቴጂዎች አንዱ ነው።

በዚህ መሰረት በኢ.ሶ.ክ.በሸቤሌ ዞን ደናን ወረዳ  የሚገኙና በዝቅተኛ ኑሮ ደረጃ የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች የወረዳው ተጠባባቂ አስተዳደሪና የጤና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መሀመድ አደን እና የወረዳው የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ ካድራ አቶሽ ኡመር  በወረዳው 10 አባወራዎች በመንደር ለመሳሰብ የታቀደ ሲሆን ለያንዳንዱ አባወራ 25 ፊየሎች᎓መኖሪያቤትና የቤት ማገልገያ ቁሳቁሶች፤ዘመናዊ  የእንስሳት እርባታ ማዕከል ከአምስት ከብቶች ጋር እንዲሁም የታረሴ እርሻ እና ለ6 ወራት ያህል የሚኖሩበት ሬሽን እንደሩዝ᎓ፓስታ᎓ዱቄትና የመሳሰሉ የምግብ አይነቶች ማስከረባቸውን አስታውቀዋል።

 በመንደር የተሰባሰቡ አባወራዎች በበኩላቸው የክልሉ መንግስት እንዲህ አይነት የመንደር ማሰባሰብ ፖሮግራም ተጠቃሚ ማድረጋቸው ያልጠበቁ መልካም አጋጣሚ እንደሆነና በተደረገላቸው ድጋፍ እጅግ ደስተኛ ከመሆናቸው ባሻገር አዲስ የኑሮ በር እንደተከፈተላቸው ገልጸዋል።በተጨማርም ሁሉም ለሰው ልጅ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮች እንደተሰጣቸውም አስረድተዋል።