መላው የኢ.ሶ.ክ. ህዝብ የክልሉን ሰላምና ልማት የሚደግፉበት ሰላማዊ ሰልፍ በሁሉም ዞኖችና ወረዳዎች አካሄዱ

ፋፈን(cakaaranews)ሰኞ፤ሚያዝያ 29/2010ዓ.ም.የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ከ10 አመታት በፊት በክልሉ በ ነበረው የሰላም እጦት ውጣ ወረዶች ምክንያት የክልሉ ዞኖች፤ወረዳዎችና ቀበሌዎች አንዱ ከሌላኛው ጋር ትስስር እንዳልነበራቸው ይታወቃል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በክልሉ ስለነበረው የንጹህ መጠጥ ውሃ እጥረት ህይወት ያለው የሰው ልጅና እንስሳትም በውሃ ጥማት ይሞቱ እንደነበር የማይካድ ሀቅ ነው።

በመሆኑም የክልሉ ህዝብ  በትንሽ አመታት ውስጥ የክልሉ መንግስትና የክልሉ መሪ ድርጅት ኢሶህዴፓ በአጠቃላይ በክልሉ ያከናወኑት የንፁህ መጠጥ ውሃ ተደራሽነት᎓የትራንስፖርት መስረት ልማት እንደ ትላልቅ ድልድዮች፤የትምህርት ተደራሽነት᎓የጤና አገልግሎት መስፋፋትና የተፋሰስና የመስኖ ግብርና እንዲሁም የወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጠራ፤የሴቶች ፖለቲካዊ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎን በማሳደጋቸውና በሁሉም ዞኖች የማይከሮፋይናንስ አገልግሎት ተደራሽ በማድረጉ እንዲሁም በቅርቡ በክልሉ አንዳንድ አከባቢዎች በኢሊኖ የአየር መዛባት ምክንያት የተከሰተውን ድርቅ አስመልክቶ የክልሉ መንግስትና የክልሉ መሪ ድርጅት ኢሶህዴፓ በሰጡት ፈጣን ምላሽ እና የመሳሰሉት መልካም ተግባራትን የሚደገፍ ሰላማዊ ሰልፍ በአጠቃላይ በክልሉ 11 ዞኖች፤93 ወረዳዎችና በ6ቱ ከተማ አስተዳደሮች በክልሉ ወጣቶች የሚመራ ሰፊ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሂዷዋል።

በመጨረሻም የተካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ የክልሉን ሰላም፣ ልማትና የአስተዳደር ሽግሸግ ህዳሴን የሚደገፍ  ሆኖ በክልሉ በተሰሩት ሁሉን አቀፍ የመሠረተ ልማት ሥራዎች እጅግ ደስተኛ መሆናቸውንና ሁሌም ከክልሉ መንግስትና ከክልሉ መሪ ድርጅት ኢሶህዴፓ ጎን እንደሚቆሙና የሃገሪቱ ጸጥታ፤ልማትና የህዳሴ ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ዘብ እንደሚቆሙ ቃል ገብተዋል።