በኢ.ሶ.መ. ፕሬዝዳንት ክቡር አብዲ መሀሙድ የሚመራ ከፍተኛ ልዑኳን ቡድን በጎርፍ ማጥለቅለቅ የተጠቁ የሙስተሂል ከተማ ነዋሪዎች እርዳታ አደረሱ

ሙስተሂል(Cakaaranews) ሰኞ፤ሚያዝያ 29/2010.በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ፕረዜዳንት ክቡር አቶ አብዲ መሀሙድ ኡመር የሚመራ ከፊተኛ የክልሉ መንግስት ልዑካን ቡድን በቅርቡ በተከታታይ ጊዜያት በክልሉ አከባቢዎች በጣለው ከባድ ዝናብ በዋቢሸቤሌ ወንዝ መሙላት በተከተለው የጎርፍ ማጥለቅለቅ  ከተጠቁ ወረዳዎች አንዷ በሆነች የሙስተሂል ከተማ ነዋሪዎች የተለያዩ የምግብ አይነቶች፤መድሃኒትና የቤት ማገልገያ ቁሳቁስ ድጋፍ አበርክቶላቸዋል። በውሃ ማጥለቅለቅ ሳቢያ የተጎዱ ዜጎች አስፈላጊው እርዳታ የሚያደርሱ የነብስ-ወከፍ ድጋፍ ሰጭ᎓የጤና አገልግሎት ሰጭ ባላሙያዎች᎓ሃኪሞች᎓የክልሉ አደጋ መከላከልና ዝግጁነት ቢሮ የቅድመ ትንቢያ ባላሞያዎች  ቡዱኖች እንዲሁም የሸቤሌ ዞን ከፍተኛ አመራር አካላትና የወረዳው ሊቀመንበርም ከፕሬዝዳንቱ ልዑካን ቡድን ጋር መሆናቸውን  ፕሬዝዳንቱ ገልጿል።

በተጨማሪም የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ክቡር አቶ አብዲ መሀሙድ ኡመር በዋቢሸቤሌ ወንዝ ዳርቻ ካሉት ወረዳዎች እንደ ቤርአኖ᎓ቀላፎ᎓ፌርፌርና ሙስተሂል ስር የሚገኙ በርካታ ቀበሌዎችና ንዑስ ቀበሌዎችም በወንዝ የውሃ ማጥለቅለቅ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው መሆናቸው በመገለፅ በተለይ ደግሞ የሙስተሂ ከተማ ነዋሪዎች ሙሉ በሙሉ ለችግሩ ሰለባ መዳረጓን አረጋግጧል። በሌላ ቡኩል የሙስተሂል ወረዳ መቀመጫ በሆነችው ሙስተሂል ከተማ በዋቢ ሸቤሌ ውሃ መሙላት በተከተለው የጎርፍ ማጥለቅለቅ ሳቢያ ከተሟ በሙሉ በውሃ መደበቋና የህዝቡ ሀብትና ንብረት እንደ መኖሪያቤቶችና የግብርና ምርቶች ሙሉ በሙሉ መወደማቸውን የክልሉ ፕሬዝዳንት አስታውቋል።

የኢ.ሶ.መ. ፕሬዝዳንት አቶ አብዲ መሀሙድ በጎርፍ የተጥለቀለቀች ሙስተሂል ከተማ የደረሰባት ችግር መጠንና ወቅታዊ ሁኔታን ለማረጋገጥና የከተማው ህዝብ ላጋጠመው ችግር ለመካፈል በከተማው ውስጥ በእግርና በጀልባ ከተዘዋወሩ በኋላ ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ዜጎች በሶስት ሄልኮብተሮችና በርካታ መኪናዎች የተጫኑና የተመላለሱበት በርካታ የምግብ ነክና የመድሃኒት እርዳታ የተበርከተላቸው ሲሆን የዋቢሸቤሌ ጉርፍ በሰውና በንብረትም ከፍተኛ ችግር ያደረሰ መሆኑን ክቡር ፕሬዝዳንቱ  አስገንዝቧል ፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ሙስተሂል ከተማ በወንዙ ዳርና ፏፋቲ ላይ መመስረቷና በከተሟ ነዋሪዎች ለበርካታ አመታት ያህል ቦታው ለከተሜነት ስልማትሜችና የከተማው ህዝብ ሁሌ ለጎርፍ ማጥለቅለቅ  አደጋ ተጋላጭ ስለሆኑ የክልሉና ብሎም የፌዴራል መንግስት ማህበረሰቡ ከቦታው እንዲነሱ ብመከርም ነገር ግን እንዳልተሳከላቸው ይታወሳል።

በዚህ መሰረት በኢ.ሶ.መ. ፕሬዝዳንት አቶ አብዲ መሀሙድ ኡመር የሚመራ የክልሉ ልዑካን ቡድን አሁን ከተሟ ያለችውበት ቦታ ለመኖር እንደማይመች ዳግም እንዲህ አይነት ችግር እንዳይከሰት ለማድረግ  ህዝቡ ወደ ሶስት ኪ.ሜ.የሚሆን አዲስ ስፍራ እንዲሰፈሩ  ከነዋሪዎች ጋር በመወያየትና ከስምምነት ከተደረሰ በኋላ የክልሉ መንግስት በቅርቡ የከተማው ፍኖተ ካርታ የሚቀየሱ ኢንጅኔሮች እንደሚላክላቸው ገልጿል።

በተያያዜም እርዳታ የተደረገላቸው ተፈናቃይ ዜጎች በበኩላቸው የክልሉ መንግስት ላደረገላቸው እርዳታ የላቀ ምስገና በማቅረብ  የፈዴራልና የክልሉ መንግስትም እንዲህ አይነት የጎርፍ ማጥለቅለቅ ችግር  ያልጠበቁ የተፈጥሮ አደጋ መሆኑን ገልጸዋል።በተጨማሪም በዋቢ ሸቤሌ ወንዝ ዳርቻ የሚገኙና የውሃ ማጥለቅለቅ አደጋ ሰለባ የሆኑት የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ወረዳዎች እንደሙስተሂል፤ቀላፎ፤ቤርኣኖና ፌርፌር የአስቹኳይ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው የክልሉ መንግስት ይፋ አደርጓል።